የኢንዱስትሪ የልማት ቀጠናን ለመቆጣጠርና ለመደገፍ የሚያስችል አዲስ አዋጅ ሊወጣ ነው

  • PDF

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 19/2004/ዋኢማ/ - የኢንዱስትሪ የልማት ቀጠናን ለመቆጣጠርና ለመደገፍ የሚያስችል አዲስ አዋጅ ሊወጣ ነው።

አዋጁ በኢንዱስትሪ ዞኖች አካባቢ የሚታዩ ችግሮችን ከመፍታቱም ባለፈ አዲስ የኢንዱስትሪ ዞኖች እንዴት እንደሚዋቀሩ ይደነግጋል ተብሏል። ለአዋጁ አተገባበር ይረዳም ዘንድ የኢንዱስትሪ ልማት ቀጠና ባለስልጣን መስሪያ ቤት ይዋቀራል።

የአዋጁ መውጣት ሃገሪቱ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ያስቀመጠችውን የኢንዱስትሪ ግብ ለማሳካት እገዛ እንደሚኖረው የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ታደሰ ሃይሌ ተናግረዋል።

ምንም እንኳ ጥናት የሚጠይቅ ቢሆንም ዛሬ ከእግር ጥፍራችን እስከ ራስ ፀጉራችን ድረስ የምንጠቀምባቸው ቁሶች በአብዛኛው ስሪታቸው የውጭ ሃገራት ናቸው ማለት ይቻላል።

ልብሳችን፤ ጫማዎቻችን መጓጓዣዎቻችንና በከፊልም ቢሆን የምንመገባቸው ምግቦች በውጭ ሃገራት የተመረቱ ናቸው።የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ታደሰ ኃይሌ እንደሚሉት ይህን ሁኔታ ለመቀየር በመንግስት በኩል የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ናቸው።  ለዚህ ደግሞ ለኢንዱስትሪ ቀጠና የሚሆኑ አካባቢዎች ተለይተው በባለሃብቶችም ሆነ በመንግስት እየለሙ ይገኛሉ።

የኢንዱስትሪ ቀጠና፤ በርካታ አምራች የቢዝነስ ተቋማት በአንድ አካባቢ ተሰባስበው የማምረት ሂደታቸውን የሚያከናውኑበት እንደሆነ የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህም በርካታ የውጭ ባለሃብቶች ወደ ሃገራችን እየገቡ በእነዚሁ የኢንዱስትሪ ቀጠናዎች የራሳቸውን የማምረቻ ፋብሪካዎችን የሚገነቡበት ሁኔታ ተፈጥሯል።





  • Facebook Page: 204028600784
  • FeedBurner: waltainfo/LdbW
  • Flickr: waltainformationcenter
  • Twitter: walta_info
  • YouTube: waltainformation
 382 guests