አሲዳማ አፈርን በማከም ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል እየተደረገ ያለው ጥረት አበረታች ውጤት ማስገኘቱ ተገለፀ

  • PDF

አዲስ አበባ ሰኔ 14/2004/ዋኢማ/ - የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩቱ አሲዳማ አፈርን በማከም የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል እያደረገ ያለው ጥረት አበረታች ውጤት ማስገኘቱን አስታወቀ።

በኢንስቲትዩቱ የአሲዳማ አፈር ተመራማሪ አቶ ጌታቸው አለሙ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንደገለፁት፤ ከሶስት አመት በፊት በተጀመረው አሲዳማ አፈርን የማከም ፕሮጀክት በመጠቀም በአርሶ አደሩ ማሳ ላይ በሄክታር 12 ኩንታል ብቻ ምርት ይገኝ የነበረውን ወደ 25 ኩንታል ማሳደግ ተችሏል።

ኢንስቲትዩቱ አሲዳማ መሬቱ ላይ የኖራ ግብዓትንና የፎስፈረስ ማዳበሪያን በመጨመር ደግሞ በሄክታር 25 ኩንታል ይገኝ የነበረውን የምርት መጠን ወደ 47 ኩንታል ማድረስ ተችሏል ብለዋል።    

አሲዳማ አፈርን ለማከም የአምስት አመት ፕሮጀክት በመንደፍ ወደ ተግባር መግባቱን ጠቁመው፤ በአሁኑ ወቅት ሶስተኛ አመቱ እየተጠናቀቀ በመሆኑ ገልፀዋል።

በቆይታውም በምርምር የተገኙ የአፈር፣ የሰብልና የሶሾ-ኢኮኖሚ መረጃዎችን ቀምሮ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት ለማቅረብ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ኢንስቲትዩቱ አሲዳማ አፈርን የማከም አዲስ ቴክኖሎጂን የቅድመ ማስተዋወቅ ስራውን በስፋት በመስራት ላይ መሆኑን ገልፀዋል።

በሀገሪቱ ከሚታረስ መሬት ውስጥ 41 በመቶ የሚሆነው ከፍተኛ፣ መካከለኛና ዝቅተኛ ደረጃ ያለው አሲዳማ አፈር እንዳለ ጠቁመው፤ ኖራን በመጠቀም የአፈሩን ምርታማነት ለማሻሻል እየተካሄደ ያለው ጥረት ውጤታማ እየሆነ ነው ብለዋል።

ኢንስቲትዩቱ በተጨማሪም አሲዳማ አፈርን ተቋቁመው ምርት ሊሰጡ የሚችሉ የሰብል ዝርያዎችን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ማላመድ የሚቻልበትን ሁኔታ ላይ ለመስራት እስትራቴጂ እቅድ መንደፉንም ተናግረዋል።







ለህዳሴ ግድብ ግንባታ የአባይን ወንዝ አቅጣጫ የማስቀልበስ ተግባር በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ይከናወናል ብለው ገምተው ነበር?




Results

የአባይን ወንዝ አቅጣጫ የማስቀልበስ ተግባር በውጭው ማህበረሰብ ዘንድ በአመዛኙ የሚፈጥረው አስተሳሰብ ምን ይመስልዎታል?





Results