19 May 2013
የግንቦት 20 በዓል በተለያዩ አገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ኢምባሲዎች ተከበረ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25/2004 (ዋኢማ ) - 21ኛው የግንቦት 20 በዓል በተለያዩ አገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ኢምባሲዎች ተከበረ ።በዓሉ በኬንያ በናይጄሪያና በሶማሌ ላንድ በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል።
ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በኬንያ ናይሮቢ በዓሉ ሲከበር ሁለቱ አገራት ለረዥም ዓመታት የዘለቀ ሰላማዊና ወንድማዊ ግንኙነት ያላቸው አገሮች በመሆናቸው በሌሎች ማህበራዊ ዘርፎች ላይ ያላቸው ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተጨባጭ እርምጃዎች እየተወሰደ መሆኑ ተመልክቷል ።
በዓሉ በናይጄሪያና በሶማሌ ላንድም በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል።
በሌላ በኩል የዘንድሮውን የግንቦት 20 በዓል ምክንያት በማድረግ የተለያዩ አገራትና መንግስታት መሪዎች ለኢትዮጵያ ህዝብ መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል ።
በዚህም መሰረት የደቡብ ኮሪያ ፣ የቱርክ ፣ የስፔንና የፓኪስታን መሪዎች መልካም ምኞታቸውን ካስተላለፉት መሪዎች ውስጥ ይጠቀሳሉ ፤ ዘገባው የኢዜአ ነው።
| < Prev | Next > |
|---|


