የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ሉሲ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የማበረታቻ ሽልማት ተበርከተለት

  • PDF

የግብፅን የሴቶች እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድንን በደርሶ መልስ 6 ለ 4 ለአሸነፈው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ሉሲ የማበረታቻ ሽልማት ግንቦት 13/2004ዓ.ም ምሽት ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በኢትዮጵያ ሆቴል ተበርክቶለታል፡፡

ለተጫዋቾች ከ3 እስከ 5 ሺህ ብር ሽልማት ያበረከተ ሲሆን ለአሰልጣኞች እና ለቡድን መሪዎች ከ3 እስከ 4 ሺህ ብር የሚደርስ ሽልማት ተሰጥቷል፡፡ በጠቅላላ 101 ሺህ ብር ወጭ ማድረጉም ተገልጿል፡፡

ከሽልማቱ በኋላም ግንቦት 18/2004 ቡድኑ ከታንዛኒያው አቻው ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ጥሩ ውጤት እንደሚስመዘግቡ ፌዴሬሽኑ ተስፋውን ገለጾ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ለቡድኑ አምበል እና አሰልጣኝ አበርክቷል፡፡

በዚሁ ጊዜም የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ሳህሉ ገብረወልድ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ሉሲ እያስመዘገበ ያለውን ውጤት በማድነቅ በቀጣይም አጠናክሮ ለመቀጠል ሁሉም የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች የሴት ቡድን እንዲኖራቸው የሚለውን መመሪያ ፌዴሬሽኑ በ2005 ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንደሚያርግ ጠቁመዋል፡፡

የቡድኑ አምበል ብዙሀን እንዳለ በበኩሏ ፌዴሬሽኑ እና የደደቢት እግር ኳስ ክለብ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል አወል ያደረጉላቸውን ድጋፍ በማመስገን ከታንዛኒያ ጋር በሚኖራቸው ጨዋታ የቡድኑ አባላት በአሸናፊነት ለመወጣት መነሳሳታቸውን ተናግራለች፡፡

33 ተጫዋቾችን በመያዝ ልምምዳቸውን ጀምረው በመጨረሻ 21 ተጫዋቾችን በቡድናቸው ማከተታቸውን የገለጹት አሰልጣኝ አብርሃም ተክለሃይማኖት ምንም እንኳ የወዳጅነት ጨዋታዎችን ለማድረግ ባይቻልም ሰፊ ጊዜ ተሰጥቶ መዘጋጀት መቻላቸው ከአለፉት ጊዜያት የተለየ እንደሚያደርገው ተናግረዋል፡፡

5 አዳዲስ ተጫዋቾችን በማካተት ከወንዶች ታዳጊ ወጣቶች ጋር ያደረጉትን 4 ጨዋታዎች በአሸናፊነት መወጣታቸውንም አሰልጣኙ ገልጸዋል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት አስፈጻሚውን በመቆጣጠር ረገድ የጀመረውን ጠንካራ እርምጃ እንዴት ያዩታል?




Results

ለህዳሴ ግድብ ግንባታ የአባይን ወንዝ አቅጣጫ የማስቀልበስ ተግባር በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ይከናወናል ብለው ገምተው ነበር




Results