ሚኒስቴሩ የሴቶችን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሳሰበ

  • PDF

አዲስ አበባ ግንቦት 8/2004/ዋኢማ/ -የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሳሰበ።
ሚኒስቴሩ የ9 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል።
ሪፖርቱን ያቀረቡት ወይዘሮ ዘነቡ ታደሰ እንዳሉት የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ በመንግስት መዋቅር በስርዓተ ጾታ ማካተቻ እንዲካተት የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው።

በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችና ጥቃቶቸን ለመከላከልና የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሚያስችሉ የተለያዩ ተግባራት መከናወናቸውንም ተናግረዋል።

ሪፖርቱን ያዳመጠው የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በበኩሉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በጉዳዩ ዙሪያ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ፤ የወጣቶችን ተሳታፊነትና ለማጠናከርና ያከናወነው ተግባር ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባው መሆኑ ጠቁሟል።

የሴቶችን ተጠቃሚነትና ተሳታፊነትን አሁን ካለው ይበልጥ ለማሳደግ ግን አሁንም የሚቀሩ ስራዎች በመኖራቸው ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ ቋሚ ኮሚቴው ማሳሰቡን የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘገባ ያመለክታል።




  • Facebook Page: 204028600784
  • FeedBurner: waltainfo/LdbW
  • Flickr: waltainformationcenter
  • Twitter: walta_info
  • YouTube: waltainformation
 164 guests