በግድቡ ላይ ምልከታ የሚያካሂድ አለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን ተቋቁሞ ስራውን በይፋ ጀመረ

  • PDF

አዲስ አበባ ግንቦት 8/2004/ ዋኢማ/- በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ ምልከታ የሚያካሂድ አለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን ተቋቁሞ ስራውን በይፋ ጀመረ።

ቡድኑ በግድቡ ዙሪያ የታችኛው የአባይ ተፋሰስ ሃገራት የሆኑት ግብጽና ሱዳን የሚያነሷቸውን ስጋቶች ለማጥራት የሚሰራ ሲሆን፤ ቡድኑ ከኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ የተወጣጡ ሁለት ሁለት ባለሙያዎች እንዲሁም 4 አለም አቀፍ ባለሙያዎችን ያካተተ ነው።

ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ተከትሎ ሁለቱ የታችኛው የአባይ ተፋሰስ ሃገራት ግብጽና ሱዳን ስጋታችን ብለው ያስቀመጧቸው ነጥቦች መሰረት በማድረግ ነው ነገሩን የሚያጣራና መተማመንን እንዲፈጥር የታለመው ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን እንዲቋቋም የተደረገው።

ሶስቱ ሃገራት ኢትዮጵያ፤ ሱዳንና ግብጽ የዛሬ ሁለት ወር ገደማ አዲስ አበባ ላይ በዚሁ ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን መቋቋም ዙሪያ ሲመክሩ ሁለቱ ሃገራት ስጋታቸውን ገልጸው ነበር።

ሱዳኖች ከደለል ጋር በተያያዘ እንዲሁም ግብጾቹ ደግሞ ከውሃ መጠን ጋር በተያያዘ ስጋታቸውን መግለጻቸውን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አቶ አለማየሁ ተገኑ አስታውሰዋል።




  • Facebook Page: 204028600784
  • FeedBurner: waltainfo/LdbW
  • Flickr: waltainformationcenter
  • Twitter: walta_info
  • YouTube: waltainformation
 263 guests