የብሄራዊ የሰብዓዊ መብቶች የሶስት ዓመታት የድርጊት መርሃ ግብር የመጀመሪያ ረቂቅ ሰነድ ውይይት እየተካሄደበት ነው

  • PDF

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2004 (ዋኢማ) - የብሄራዊ የሰብዓዊ መብቶች የሶስት ዓመታት የድርጊት መርሃ ግብር የመጀመሪያ ረቂቅ ሰነድ ከትናንት ጀምሮ በተባበሩት መንግስታት የስብሰባ አዳራሽ ውይይት እየተካሄደበት ነው።

ሰነዱ ከዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ጋር ተጣጥሞ የሚሄድ ሲሆን እየተካሄደ ያለው ውይይትም ድርጊት መርሃ ግብሩን ለማስተካከልና ለማዳበር በብሄራዊ የሰብዓዊ መብቶች የድርጊት መርሃ ግብር ዝግጅት ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት የተዘጋጀ ነው።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ጥሩነህ ዜና የእቅዱ መዘጋጀት በህገ መንግስቱ ላይ የተረጋገጡትን መሰረታዊ የሰብዓዊ መብቶችንና ነፃናቶችን በበለጠ ለማጠናከር ያግዛል ብለዋል።

ሊተገበሩ የሚችሉና ችግር ፈቺ የሆኑ 24 መብቶችን የያዘው ይኸው ረቂቅ ሰነድ በተሳታፊዎች ውይይት ዳብሮ ከ2005 እስከ 2007 ድረስ ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው ውይይት ላይ ከ200 የሚበልጡ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉበት እንደሆነ የዘገበው ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ነው።

  • Facebook Page: 204028600784
  • FeedBurner: waltainfo/LdbW
  • Flickr: waltainformationcenter
  • Twitter: walta_info
  • YouTube: waltainformation
 326 guests