አዳዲስ የመፍትሔ ሀሳቦችን ተግባራዊ በማድረግ ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለጸ

  • PDF

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 2/2004/ዋኢማ/ - ችግር ፈቺ የሆኑ አዳዲስ የመፍትሄ ሀሳቦችን ተግባራዊ በማድረግ በአፍሪካ ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥ እንደሚቻል ተገለፀ ።

22ኛው የዓለም የኢኮኖሚ ጉባዔ ዛሬ በሸራተን አዲስ ተጀምሯል። ከዋናው ጉባዔ በተጓዳኝ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይም ውይይት እየተደረገ ነው።

መልካም አስተዳደር ለዘላቂ ልማት እንደ አዲስ መፍትሔ በሚል ርዕሰ ጉዳይ በአዋሽ አዳራሽ በተደረገ ውይይት በአፍሪካ ፈጠራን በማበረታታት፤ የመሰረተ ልማቶችን በማስፋፋት ዘላቂ ልማት ማምጣት እንደሚቻል ተጠቁሟል።


የወጣቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ ማሳደግ፣ የተፈጥሮ ሀብትን በአግባቡ መጠቀም፣ የእርሻውን ዘርፍ በማሳደግ የምግብ ዋስትና ብሎም አጠቃላይ ኢኮኖሚን ማረጋገጥና ሙስናን መዋጋት  ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም በውይይቱ ወቅት ተገልጿል።

ተወያዮቹ በአፍሪካ ዘላቂ ልማትን ለማምጣት የዕድገት ማነቆ የሆኑ ችግሮችን መፍታት ወሳኝ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተው ተወያይተዋል።

በአህጉሪቱ አዳዲስና ችግር ፈቺ የሆኑ የመፍትሄ ሀሳቦችን በማመንጨትና ተግባር ላይ በማዋል ልማትን ማፋጠን እንደሚቻልም ገልፀዋል።

በአፍሪካ ካለው የህዝብ ብዛት ከ30 በመቶ በላይ የሚሆኑት ዕድሜያቸዉ ከሰላሳ አመት በታች የሆኑ ወጣቶች መሆናቸውን የጠቆሙት ተወያዮቹ የወጣቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ ማጠናከር እንደሚገባም አሳስበዋል።

ወጣቶችን በማሳተፍ በተለይ አመራሮች ትልቅ ሀላፊነትና ተጠያቂነት እንዳለባቸው ያስገነዘቡ ሲሆን፤ የወጣቶች ተሳትፎ ሙስናን ለማስወገድና ለሀገር ልማት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረዉም ተጠቁሟል።

በውይይቱ ላይ ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ የመንግስት ተወካዮችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።














ለህዳሴ ግድብ ግንባታ የአባይን ወንዝ አቅጣጫ የማስቀልበስ ተግባር በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ይከናወናል ብለው ገምተው ነበር?




Results

የአባይን ወንዝ አቅጣጫ የማስቀልበስ ተግባር በውጭው ማህበረሰብ ዘንድ በአመዛኙ የሚፈጥረው አስተሳሰብ ምን ይመስልዎታል?





Results