የኢህአዴግ የስራ ሃላፊዎች ከአፍሪካ አገራት አምባሳደሮች ጋር ተወያዩ

  • PDF

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 26 2004 (ዋኢማ) - ከፍተኛ የኢህአዴግ የስራ ሃላፊዎች ከአስራ ሶስት የአፍሪካ አገራት አምባሳደሮች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ትናንት ተወያዩ፡፡

ከአስራ ሶስት የአፍሪካ አገራት አምባሳደሮች ጋር በኢህአዴግ ጽሕፈት ቤት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተደረገውን ውይይት የመሩት የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሬድዋን ሁሴን እና የኢህአዴግ የህዝብና የውጪ ግንኙነት መምሪያ ሃላፊ አቶ ሴኩቱሬ ጌታቸው ናቸው።

በውይይቱ ላይ ከሱዳን፣ሶማሊያ፣ኬኒያ፣ ሩዋንዳ፣ ዩጋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ዛምቢያ፣ሞዛምቢክ፣ደቡብ አፍሪካ፣ ናሚቢያ፣ ናይጄሪያ፣ ጋና እና አልጄሪያ ኤምባሲዎችን የወከሉ አመባሳደሮች  ተካፍለዋል፡፡

ውይይቱ በዋናነት ኢህአዴግ በወቅቱ በማከናወን ላይ ያለውን ውስጣዊ እንቅስቃሴ፣ እንዲሁም አባላትንና ህዝብን በማስተባበር ልማትና ዴሞክራሲን ለማረጋገጥ እንደ ፓርቲ እያደረገው ያለውን ጥረት በማብራራት ላይ ያተኮረ ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ኢህአዴግ የአፍሪካን ልማት ለማረጋገጥ የተለያዩ የአፍሪካ ፓርቲዎች በጋራ መስራት እንዳለባቸው ከዚህ አኳያ ኢህአዴግ ከበርካታ የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የጠበቀ ግንኙነት መፍጠሩን እንዲሁም ሌሎች ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን አቶ ሬድዋን ለአምባሳደሮቹ  አብራርተዋል ፡፡

አምባሳደሮቹ በበኩላቸው ኢህአዴግ ሰላም፣ዴሞክራሲና ልማትን ለማረጋገጥ እየተጫወተ ያለው የመሪነት ሚና ሊደነቅ የሚገባው መሆኑንና በርካታ ጠቃሚ ልምዶችን የቀሰሙ መሆናቸውን ገልፀው  በአገሮቻቸው መንግስታትና ህዝቦች መካከል ግንኙነቱን ለማጠናከርና በፓርቲዎች መካከል ያለውን  ግንኙነት ለማገዝ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልፀዋል፡፡

አምባሳደሮቹ በአገራቱና በህዝቦች መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከርና የህዝቦችን የጋራ ጥቅም ለማራመድ እስካሁን ያደረጉትን ጥረት አቶ ሬድዋን አድንቀው ወደፊት ይህንኑ ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል፡፡

ኢህአዴግ ከሩዋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ዩጋናዳ፣ ታንዛኒያና አልጄሪያ ፓርቲዎች ጋር የጠበቀ የስራ ግንኙነት  እንዳለው ይታወቃል፡፡

  • Facebook Page: 204028600784
  • FeedBurner: waltainfo/LdbW
  • Flickr: waltainformationcenter
  • Twitter: walta_info
  • YouTube: waltainformation
 196 guests