21 May 2013
ዓለም ዓቀፉ ማኅበረሰብ ለኮሞሮስ አስቸኳይ እርዳታ እንዲሰጥ የአፍሪካ ኅብረት ጠየቀ
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 24/2004 (ዋኢማ) - ዓለም ዓቀፉ ማኅበረሰብ በኮሞሮስ በተከሰተው አስከፊ የአየር ጸባይ ሳቢያ ለደረሰው ችግር አስቸኳይ እርዳታ እንዲሰጥ የአፍሪካ ኅብረት ጠየቀ፡፡
የኅብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ዶክተር ዣን ፒንግ ባለፉት ሳምንታት በአገሪቱ በተከሰተው አስከፊ የአየር ጸባይ ሳቢያ በርካቶች መሞታቸውንና ከፍተኛ ውድመት መድረሱን ገልጸዋል፡፡
ይህን ችግር ለመታደግ የአፍሪካ ኅብረት አባል አገራትና ዓለም ዓቀፉ ማኅበረሰብ አስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
እንደ ኢዜአ ዘገባ የአፍሪካ ኅብረት በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ለኮሞሮስ ሕዝብና መንግሥት ያለውን አጋርነት ይገልጻል ብለዋል፡፡
| < Prev | Next > |
|---|


