ኢትዮጵያ በጎረቤት አገራት ሰላም ለማሰፈን በምታከናውነው ተግባር የመን በትብብር ለመሥራት ፍላጎት አላት

  • PDF

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 24/2004 (ዋኢማ) - ኢትዮጵያ በጎረቤት አገራት ሰላም ለማስፈን በምታከናውነው ተግባር የመን በትብብር ለመሥራት ፍላጎት እንዳላት ገለጸች።

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ዛሬ ማምሻውን በጽሕፈት ቤታቸው ከየመን ፕሬዚዳንት አብዱ ራቡህ ማንሱር አል-ሃዲ የተላከ መልዕክት ከአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የፕሬዚዳንቱ ልዩ መልዕክተኛ ከሚስተር አቡበከር አብዱላሂ አል-ኪርቢ ተቀበሉ፡፡

ሚስተር አብዱላሂ አል-ኪርቢ ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ጋር ባደረጉት ውይይት ኢትዮጵያ በአካባቢው ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም የኢኮኖሚ ትብብርን ለማጠናከር በምታከናውነው ተግባር የመን በጋራ ለመሥራት ፍላጎት አላት።

በየመን ሰላም መደፍረስ ምክንያት ባለፉት ሁለት ዓመታት በሁለቱ አገራት መካከል የነበረው ታሪካዊ ግንኙነት የተቀዛቀዘ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ሰላም የሰፈነ በመሆኑ እንደገና በሚጠናከርበት ጉዳይ ላይ ምክክር ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

እንዲሁም በአካባቢ ሰላም ላይ የሚመክረው የሰንዓ ፎረም በሚጠናከርበት ጉዳይ ላይም ባለስልጣናቱ ውይይት አድርገዋል።

በሁለቱ አገራት መካከል በኢኮኖሚና ሽብርተኝነትን በመዋጋት የመን ከኢትዮጵያና ከሰንዓ ፎረም አባል አገራት ጋር በትብብር ለመስራት ፍላጎት አላት ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት የየመን የፖለቲካ መደፍረስ በዜጎቿ የሚፈታ ጉዳይ ቢሆንም ለአገሪቱ ሰላም መስፈን ኢትዮጵያ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት።

የመን ለኢትዮጵያ ቅርብ ጎረቤት አገር በመሆኗ በአገሪቱ ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ ሰላማዊ እንዲሆን በትኩረት ሰጥታ እንደምትሰራም ገልጸዋል።

በኢትዮጵያና በየመን መካከል የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር ለመፍጠር ሁለቱም አገራት እንቅስቃሴ ለማድረግ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

የሁለቱን አገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት በተጠናከረ መልኩ ለመቀጠል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ የሃሳብ ልውውጥ አድርገዋል።

እንዲሁም በየመን የውስጥ ጉዳይና በአፍሪካ ቀንድና በአካባቢው አገራት ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂደዋል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ የሰንዓ ፎረም አባል አገራት ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን፣ ጅቡቲና የመን ናቸው።

  • Facebook Page: 204028600784
  • FeedBurner: waltainfo/LdbW
  • Flickr: waltainformationcenter
  • Twitter: walta_info
  • YouTube: waltainformation
 232 guests