በክልሉ በተለያዩ የማዕድን ሥራ ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎችና ግለሰቦች ከ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል አስመዝግበዋል

  • PDF

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 24/2004 (ዋኢማ) - በትግራይ ክልል በወርቅና በተለያዩ የማዕድን ሥራ ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎችና ግለሰቦች ከ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ማስመዝገባቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አስታወቁ።

ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ አባይ ወልዱ ትላንት በሽሬ እንደ ሥላሴ በተካሄደው ሁለተኛው አገር አቀፍ የባህላዊና አነስተኛ ደረጃ ማዕድን አምራቾች የልምድ ልውውጥ ጉባኤ ላይ እንደተናገሩት ማዕድን አምራቾቹ ከተሰማሩባቸው የማዕድን ምርቶች መካከል ወርቅ፣ አሸዋ፣ ድንጋይና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡

ክልሉ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የሚያካሄደውን የቅንጅት ስራ በማጠናከር ለባህላዊና አነስተኛ ደረጃ የማዕድን አምራቾች የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የዞን፣ የወረዳና የቀበሌ መስተዳደር አካላት ማዕድን አምራቾችን በማሰተባበርና በመደገፍ የተፈጥሮ ሀብትን በማይጎዳ መልኩ እንዲሰሩ ክትትል በማድረግ ረገድ የተሻለ እንቅስቃሴ እያካሄዱ መሆኑን አስረድተዋል።

በመሆኑም በማዕድን ማምረት ስራው ላይ ከ30 በላይ ኩባንያዎችና ከ100 ሽህ በላይ ግለሰቦች ከክልሉ ማዕድንና ኢነርጂ ኤጄንሲ ፍቃድ ወስደው በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

ክልሉ በተለያዩ ማዕድናት የከበረ ቢሆንም እስካሁን በልማት ላይ የዋለው ግን በጣም አነስተኛ ሲሆን 90 በመቶ የሚሆነው የኮንስትራክሽን ማዕድን መሆኑን ገልጸዋል፡፡

እንደ ኢዜአ ዘገባ በተለይ በወርቅ ማምረት ስራ ላይ ከተሰማሩት ወጣቶች መካከል መምህር አብርሃሌ ገብረህይወት፣ ሺሻይ ምናሴና ፍሰሃ ገብረኢየሱስ በሰጡት አስተያየት ከዘርፉ በሁለት ወር እሰከ 30 ሽህ ብር ገቢ አግኝተዋል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት አስፈጻሚውን በመቆጣጠር ረገድ የጀመረውን ጠንካራ እርምጃ እንዴት ያዩታል?




Results

ለህዳሴ ግድብ ግንባታ የአባይን ወንዝ አቅጣጫ የማስቀልበስ ተግባር በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ይከናወናል ብለው ገምተው ነበር




Results