24 May 2013
የዓለም ታዋቂ የፊልም ፕሮዲዩሰሮች፣ ተዋናዮችና የታዋቂ መጽሔቶች አዘጋጆች ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 22/2004 (ዋኢማ) - በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከፍተኛ ዲፕሎማት የሚመሩ የዓለም ታዋቂ የፊልም ፕሮዲሰሮችና ተዋናዮች ኢትዮጵያን ሊጎበኙ እንደሆነ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጸው ቁጥራቸው ከ45 በላይ የሚሆኑ ታዋቂ እንግዶች በቆይታቸው አዲስ አበባን፣ ቢሾፍቱ ከተማ የሚገኙ የተለያዩ ሪዞርቶች እና በአማራ ክልል የባህር ዳርንና የላሊበላን ታሪካዊ ቦታዎችን ይጎበኛሉ፡፡
ኢትዮጵያን የሚጎበኙት በዓለም ታዋቂ የሆኑት "ኦፔራ ማጋዚን፣ ኤልስ ማጋዚን፣ የዓለም ሞዴል ሴትና ወንድ አርቲስቶችና የፊልም ፕሮዲዩሰሮች ናቸው፡፡
የእንግዶቹ ጉብኝት ለአገሪቱ የገፅታ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለውም ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡
ለእንግዶቹ ዛሬ ማታ በቦሌ ዓለም ዓቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል እንደሚያደርጉላቸው አመልክቷል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
| < Prev | Next > |
|---|


