የኮንሶ ባህላዊ መልክዓ ምድር አገሪቱ ለተፈጥሮ ሀብት ልማትና አካባቢ ጥበቃ ሥራ ለሰጠችው ትኩረት ተምሳሌት ነው

  • PDF

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 22/2004 (ዋኢማ) -  ኢትዮጵያ ለተፈጥሮ ሀብት ልማትና ለአካባቢ ጥበቃ ሥራ ለሰጠችው ትኩረት በኮንሶ ባህላዊ መልክአ ምድር ላይ ያሉ ቅርሶች ጥሩ ተምሳሌት መሆናቸውን የኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

በባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወይዘሮ ቀለሟ መኮንን እንደተናገሩት የካንሶ ህዝብ ተራሮቻቸውን ለማልማት የሰሩት የእርሻ ላይ እርከንና የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራዎች ለሁሉም የአገሪቱ አርሶ አደሮች መልካም ተምሳሌት የሚሆን ነው፡፡

መካነ ቅርሶቹ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት /ዩኒስኮ/ የተመዘገበበት የአንደኛ ዓመት በዓልም ኮንሶና አካባቢውን የቱሪስት መዳረሻነት የበለጠ ከማጠናከሩም በላይ ለአርሶ አደሩ ታታሪነትና ጥንካሬ እውቅና የሚያስገኝ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የደቡብ ክልል የኘሬዚዳንት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወይዘሮ ንጋቷ ማቲዎሽ በበኩላቸው የኮንሶ ህዝብ ለቅርስ ጥበቃና እንክብካቤ ያላቸውን ጥንካሬና ለባህላቸው እድገት ከሚያደርጉት ትግል ሁሉም መማር እንዳለበት አመልክተዋል፡፡

የኮንሶ ብሄረሰብ የማንነታቸው መገለጫ የሆኑ የተለያዩ ባህላዊና ታሪካዊ እሴቶቻቸው ሳይበረዝ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲሸጋገር ያደረጉት እውነታም የሚደነቅ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ዩኔስኮ የኮንሶን ባህላዊ የመልክዓ ምድር ሁኔታን ታሪካዊ ቅርስ ሆኖ በዓለም መዝገብ ላይ እንዲመዘገብ ያደረገው እ.አ.አ ሐምሌ 2011መሆኑ የሚታወስ ነው ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

  • Facebook Page: 204028600784
  • FeedBurner: waltainfo/LdbW
  • Flickr: waltainformationcenter
  • Twitter: walta_info
  • YouTube: waltainformation
 322 guests