ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለ1 መቶ 44 ሺ ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩን የአማራ ክልል ገለጸ

  • PDF

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2004 (ዋኢማ) - በአማራ ክልል ባለፉት 9 ወራት በጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ዘርፍ 1 መቶ 44 ሺህ ለሚሆኑ ሰዎች  የስራ ዕድል መፈጠሩን የክልሉ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲ አስታወቀ።

የኤጀንሲው የህዝብ ግንኙነት ዋና የስራ ሂደት  አቶ ዘላለም ንጉሴ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንደገለፁት፤ባለፉት 9 ወራት  ለ58 ሺ 515 ሰዎች ቋሚና ለ86 ሺ  153 ሰዎች ጊዜያዊ የስራ እድል ተፈጥሯል።

እንደ አቶ ዘላለም ማብራሪያ የሥራ እድሉ የተፈጠረው በትልልቅ የመንግስት ፕሮጀክቶች፣ በመካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች፣ በኮንስትራክሽን፣ በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ በከተማ ግብርና፣ በንግድ እና በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የልማት ዘርፎች ነው።

የሥራ እድሉ ከተፈጠረላቸው መካከል 47 ሺ 701 የሚሆኑት ሴቶች እንደሆኑ የጠቆሙት የህዝብ ግንኙነት ባለሙያው ይህም ሴቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ የልማት ተጠቃሚነታቸውና ተሳትፎአቸው እየጨመረ መምጣቱን ያሳያል ብለዋል።

በዘንድሮው የበጀት ዓመት መጨረሻ ላይ በክልሉ 274 ሺ 101 ለሚሆኑ ሰዎች የስራ እድል ለመፍጠር መታቀዱን የጠቆሙት አቶ ዘላለም ለሥራ ዕድሉ መፈጠር የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ስትራቴጂ ጠቀሜታ የጎላ መሆኑንም አመልክተዋል።

አንቀሳቃሾች ከጥገኝነት አስትሳሰብ በመላቀቅ የቅድመ ብድር ቁጠባን ማጐልበታቸውና ሠርቶ መለወጥን እንደባህል መውሰዳቸው ለስራ እድሉ መፈጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ መፍጠሩን ተናግረዋል።

  • Facebook Page: 204028600784
  • FeedBurner: waltainfo/LdbW
  • Flickr: waltainformationcenter
  • Twitter: walta_info
  • YouTube: waltainformation
 198 guests