ሕንድ የረጅም ርቀት ተወንጫፊ ሚሳይል ሞከረች

  • PDF

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 15/2004 (ዋኢማ) - ሕንድ የኑክሌር አረር ሊሸከም የሚችል የረጅም ርቀት ተወንጫፊ ሚሳይል ሙከራ ማካሔዷን ኤኤፍፒ ከኒውዴልሂ ያስተላለፈው ዜና አመለከተ። ይኸው የረጅም ርቀት ተወንጫፊ (ቦሊስቲክ) ሚሳይል «አግኒ ፋይቭ» የሚል ስም ተሰጥቶታል።

ሕንድ ከትናንት በስቲያ የሞከረችው «አግኒ ፋይቭ ሚሳይል» 5000 ኪሎ ሜትር (3,100m ማይልስ) ርቀት መሸፈን እንደሚችል ተገልጿል። ይህ የረጅም ርቀት ተወንጫፊ ሚሳይል በሕንድ ዘንድ የኑክሌር ጥቃትን ለመከላከል እንደማዕዘን ድንጋይ ተደርጐ የተወሰደ መሆኑን የኤኤፍፒ ዘገባ ጨምሮ ገልጿል።

ሕንድ እ.አ.አ በ2010 «አግኒ-ቱ» የተባለ የመካከለኛ ርቀት ማለትም 2000 ኪሎ ሜትር (1,250 ማይልስ) ተወንጫፊ ሚሳይል ሙከራ ማካሄዷ ተገልጿል። ሕንድ «አግኒ-ፋይቭ» የሚል ስም የሰጠችውን የኑክሌር አረር ሊሸከም የሚችል የረጅም ርቀት ሚሳይል በኦሪሳ ግዛት በምትገኘው ዊለር ደሴት አካባቢ የሞከረችው ትናንት ነው።

ሙከራው በተሳካ ሁኔታ መካሔዱን መነሻ በማድረግ የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ማንሞሐን ሲንግ ሚሳይሉን ለሠሩት ሳይንቲስቶች የደስታ መግለጫ መልዕክት ማስተላለፋቸው ተገልጿል።
አሁን በሕንድ የተሞከረው ዓይነት የረጅም ርቀት ተወንጫፊ ሚሳይል ያላቸው አገሮች ቻይና፣ ሩሲያ፣ ፈረንሳይ፣ አሜሪካና ብሪታኒያ ብቻ መሆናቸው ታውቋል።

  • Facebook Page: 204028600784
  • FeedBurner: waltainfo/LdbW
  • Flickr: waltainformationcenter
  • Twitter: walta_info
  • YouTube: waltainformation
 167 guests