የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር በማሊ የተያዙት ባለሥልጣናት በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጠየቁ

  • PDF

አዲስ አበባ፤  ሚያዝያ 12/2004 (ዋኢማ) - የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር ዶክተር ዣን ፒንግ በማሊ በቁጥጥር ሥር የዋሉት የአገሪቱ ሲቪልና ወታደራዊ ባለሥልጣናት በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጠየቁ፡፡

ኅብረቱ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጸው ዶክተር ፒንግ በማሊ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በቅርብ እየተከታተሉት ነው፡፡

ሊቀመንበሩ በአገሪቱ በርካታ ሲቪልና ወታደራዊ ባለሥልጣናት በቁጥጥር ሥር መዋላቸው እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል፡፡

በማሊ በርካታ ሲቪልና ወታደራዊ ባለሥልጣናት በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ሰብዓዊ መብታቸውን የሚጥስና የሚወገዝ ተግባር እንደሆነ ጠቅሰው በአስቸኳይ እንዲለቀቁም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ይህ ተግባር በማሊ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለመመለስና በአገሪቱ ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት የሚያደናቅፍና በቅርቡ የተደረሰውን ስምምነት የሚጥስ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

  • Facebook Page: 204028600784
  • FeedBurner: waltainfo/LdbW
  • Flickr: waltainformationcenter
  • Twitter: walta_info
  • YouTube: waltainformation
 214 guests