ቀነኒሳ በአየርላንድ የ10 ኪሎ ሜትር ሩጫ አሸነፈ

  • PDF

አዲስ አበባ, ሚያዝያ 8 ቀን 2004 (አዲስ አበባ) - አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ትናንት በአየርላንድ ባደረገው የ10ኪሎ ሜትር ሩጫ የአውሮፓን የርቀቱን ክብረ ወሰን በመስበር አሸነፈ።

ኢዜአ የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር እንዳስታወቀው ቀነኒሳ በደብሊን ከተማ ያካሄደውን ውድድር በ27ደቂቃ ከ49ሰከንድ አጠናቋል።

ይህም በአየርላንድ ከ28 ደቂቃ በታች ሲገባ የመጀመሪያው አድርጎታል።

ላለፉት ሁለት ዓመታት ከግማሽ ከሕመም ጋር ሲታገልና ከአራት ወራት በፊት በ11ኛ ደረጃ ውድድር ካጠናቀቀበት ሁኔታ ወጥቶ ያስመዘገበው ውጤት ዛሬም በተወዳዳሪነት ውስጥ እንደሚገኝ ያስመሰከረበት መሆኑን ማህበሩ አመልክቷል።

የሃያ ዘጠኝ ዓመቱ ቀነኒሳ ሁለተኛ የወጣውን አያድ ላምዳሳም የተባለውን ስፔናዊ በአንድ ደቂቃ ቀድሞታል።ጣልያንያዊው ዳንኤሌ ሙኢቺ ሦስተኛ ወጥቷል።

ቀነኒሳ ከሦስተኛው ኪሎ ሜትር ጀምሮ ውድድሩን በመምራት ተፎካካሪዎቹ ተከትለውት ብቻ እንዲሮጡ ማድረጉን ዘገባው አመልክቷል።

ወደ ውድድሩ የመጣሁት ማንንም ለማስበርገግ ሳይሆን በውድደሩ ያለኝን አቋም ለመለካት ነው በማለት ቀነኒሳ መናገሩን ምንጩን ጠቅሶ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት አስፈጻሚውን በመቆጣጠር ረገድ የጀመረውን ጠንካራ እርምጃ እንዴት ያዩታል?




Results

ለህዳሴ ግድብ ግንባታ የአባይን ወንዝ አቅጣጫ የማስቀልበስ ተግባር በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ይከናወናል ብለው ገምተው ነበር




Results