የጂንካ ሆስፒታል የማስፋፊያ ግንባታዎችን በማካሄድ ላይ ነው

  • PDF

ጂንካ፤ ሚያዝያ 6 2004 /ዋኢማ/ - የጂንካ ሆስፒታል ለሕሙማን የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት በአራት ሚሊዮን ብር ወጪ የማስፋፊያ ግንባታ በማካሄድ ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡

የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ተወካይ ዶክተር ረድኤት ረጋሳ ለዋልታ እንዳስታወቁት የማስፋፊያ ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘው የክልሉ መንግሥት በመደበው የአራት ሚሊዮን ብር ወጪ ነው፡፡

ባለፈው ዓመት የተጀመሩትና በተያዘው ዓመት መጨረሻ የሚጠናቀቁት የማስፋፊያ ግንባታዎች እያንዳንዳቸው 48 የሕሙማን አልጋዎችን የመያዝ አቅም ያላቸው ሁለት ሕንጻዎች መሆናቸውን ዶክተር ረድኤት ገልጸዋል፡፡

የግንባታው መካሄድ  ሆስፒታሉ በአሁኑወቅት ባለበት የክፍል ጥበት የተነሳ ሕሙማንን አስተኝቶ ለማካም ያለበትን ችግር ለመፍታት እንደሚያስችለው ዶክተር ረድኤት  አስረድተዋል፡፡

ሆስፒታሉ የነበረበትን የቀዶ ሕክምና ዶክተሮች እጥረት ለማቃለል የተለያዩ ጥረቶችን በማድረጉ ችግሩ በአሁኑወቅት መቀረፉን የገለፁት ተወካዩዋ በአሁኑ ወቅት ዘጠኝ ኢትዮጲያዊያንና ሦስት የደቡብ ኮሪያ ዶክተሮች አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ አመልክተዋል፡፡

የጂንካ ሆስፒታል በአሁኑ ወቅት በ 18 አይነት የሕክምና ዘርፎች አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ከዶክተር ረድኤት ገለጻ ለመረዳት ተችሏል፡፡

  • Facebook Page: 204028600784
  • FeedBurner: waltainfo/LdbW
  • Flickr: waltainformationcenter
  • Twitter: walta_info
  • YouTube: waltainformation
 175 guests