19 May 2013
በአፍሪካ የተካሄዱት ምርጫዎች ውጤታማ ናቸው - የአፍሪካ ኅብረት
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 6/2004 (ዋኢማ) - የአፍሪካ ኅብረት በአሕጉሩ በተለያዩ አገራት የተካሄዱት ምርጫዎች ውጤታማ እንደሆኑ አስታወቀ፡፡
የኅብረቱ የሠላምና ጸጥታ ምክር ቤት ትናንት ያካሄደውን 317ኛ ስብሰባ ሲያጠናቅቅ ባወጣው መግለጫ በሴኔጋል የተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤታማ በመሆኑ ለሴኔጋል ሕዝብና መንግሥት የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
በግብጽ የተካሄደው የፓርላማ ምርጫና በጊኒ ቢሳኡ የተካሄደው የመጀመሪያ ዙር ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በሠላማዊ መንገድ መጠናቀቁን አስታውቋል፡፡
የጊኒ ቢሳኡ ሁሉም ወገኖች ሁለተኛው ዙር ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በሠላማዊ መንገድና ግልጽነት በተሞላበት ሁኔታ እንዲካሄድ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡
በጋምቢያ የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በተመለከተም ውይይት ማካሄዱን ገልጿል፡፡
በአልጄሪያና በሌሴቶ በግንቦት ወራት ለሚካሄዱት የፓርላማ አባላት ምርጫ ታዛቢዎችን እንደሚልክም አስታውቋል፡፡
የአፍሪካን የዴሞክራሲ፣ የምርጫና አስተዳደር ቻርተርን ያላጸደቁ አገራት ቻርተሩን እንዲያጸድቁም ጥሪ አቅርቧልሲል ኢዜአ ዘግቧል።
| < Prev | Next > |
|---|


