ኮሚሽኑ ከ27 ሺህ በላይ የተመራጮችና የመንግሥት ሠራተኞችን ሃብት መዘገበ

  • PDF

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 6/2004 (ዋኢማ) - የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን እስካሁን ከ27 ሺህ በላይ የተመራጮችና የመንግሥት ሠራተኞችን ሃብት መመዝገቡን አስታወቀ፡፡
ኮሚሽኑ በልማትና በመልካም አስተዳደር ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ ሙስናና ብልሹ አሰራሮች ለመዋጋት ትኩረት ሰጥቷል።

የኮሚሽኑ የሥነ ምግባር ትምህርትና ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ አሰፋ ለኢዜአ እንደተናገሩት ሙስናን ለመከላከል በሚደረገው እንቅስቃሴ የተሿሚዎች፣ የተመራጮችና የመንግሥት ሠራተኞችን ሃብት ማሳወቅና ማስመዝገብ ምዝገባ አከናውኗል፡፡

ኮሚሽኑ ባደረገው ምዝገባ ባለፉት ስድስት ወራት 11 ሺህ 856 ተመራጮችና የመንግሥት ሠራተኞችን ሀብት መመዝገቡን አስረድተዋል።

የመንግሥትን አሠራር በግልጽነትና ተጠያቂነት መርህ ላይ የተመሠረተ በማድረግ በመንግሥትና በሕዝብ መካከል መተማመን እንዲሰፍን ያደርጋል ምዝገባው መከናወኑንና በዚህም ከ13 ሺህ በላይ የሚሆኑትን መረጃ በማጣራት ሰርተፍኬት ሊሰጣቸው የሚገባውን የመለየትና መረጃዎች እንዲያሟሉ ተደርጓል፡፡

ከመካከላቸም የአምስት ሺህ ሃብት አስመዝጋቢዎች የሰርተፍኬት ዝግጅትመጠናቀቁንም ዳይሬክተሩ አመልክተዋል፡፡

ኮሚሽኑ በልማትና በመልካም አስተዳደር ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ ሙስናና ብልሹ አሰራሮች ላይ ትኩረት በማድረግ እየተንቀሳቀሰ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

በእድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ በመልካም አስተዳደርና የዲሞክራሲ ግንባታ ዘርፍ ግልጽነትን ማስፈንና ሙስናን ከምንጩ ማድረቅ በአገር አቀፍ ደረጃ ትኩረት ከተሰጣቸው ዓበይት ጉዳዮች መካከል አንዱ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ኮሚሽኑ ወደፊት የፀረ ሙስና ትግል በሰፊው ሕዝባዊ መሠረት ላይ በመጣል የፀረ ሙስና ሠራዊት ግንባታ በማካሄድ ትግሉን ይበልጥ ለማጠናከርና ለማስፋፋት ጥረት እንደሚያደርግ አቶ ብርሃኑ አስታውቀዋል፡፡

በቀጣይ ልማትና በመልካም አስተዳደር ሥርዓት ግንባታ ሂደት ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ ተብለው በተለዩ የመሬት አስተዳደር ፣ የፋይናንስ፣ ግብርና ታክስ አስተዳደር፣ ከፍተኛ የመንግሥት ግዢና ሽያጭ እንዲሁም በፍትህ አስተዳደር አካላት ዙሪያ የተጠናከረ ትግል እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

  • Facebook Page: 204028600784
  • FeedBurner: waltainfo/LdbW
  • Flickr: waltainformationcenter
  • Twitter: walta_info
  • YouTube: waltainformation
 104 guests