24 May 2013
የለንደን ኦሊምፒክ ተስፋን የሚያሟጥጥ ውጤት?
እየተካሔደ ባለውና ዛሬ በሚጠናቀቀው የዴጉው 13ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ እያስመዘገበችው ያለው ውጤት አነጋጋሪ ሆኗል፡፡
ገናን ከነበረችበትና ጎረቤቷንና ዋነኛ ተቀናቃኟን ኬንያን ሁሉ በልጣ በነበረችበት የረዥም ርቀት (5ሺሕ እና 10ሺሕ) እና ማራቶን ከ10 ሺው የኢብራሂም ጄይላን ወርቃዊ ድል በስተቀር (እስከዓርብ ምሽት ድረስ በነበረው ውጤት) በሌሎቹ ድሉ ርቋት ሰንብቷል፡፡ በመክፈቻው ዕለት በተደረጉት የሴቶች 10ሺ የመጀመርያውን አራት ደረጃዎች፣ በማራቶንም እንደዚሁ የመጀመርያዎቹን ሦስት ደረጃዎች ኬንያውያኑ አላስቀመሷትም፡፡
ከትናንትና በስቲያ በሴቶች 5ሺሕ ኬንያውያቱ ኢትዮጵያ ቀድሞ ትታወቅበት የነበረውን የቡድን ሥራ ነጥቀዋት ወርቁንና ብሩን ያገኙበትን የመጀመርያውን ሁለት መስመር ወስደዋል፡፡ ከሰባት ዓመት በፊት የአቴንስ ኦሊምፒክን የ5ሺሕ ወርቅ አሸናፊዋ መሠረት ደፋር ታግላ መስመሩን ማለፍ የቻለችው ነሐስ ሜዳይ ያሰጣትን 3ኛነቱን ብቻ ነው፡፡
ኬንያ በአዳዲስ ተተኪ አትሌቶቿ በብዛት በየውድድር መድረክ እያስመዘገበችው ያለውና በዲሲፕሊን የታገዘ የአመራር ውጤት ከላቀ ውጤት ላይ እያስቀመጣት ነው፡፡ እስከ ዓርብ ምሽት በነበረው የዓለም ሻምፒዮና ውጤቷ በአምስት ወርቅ ከአሜሪካ ቀጥላ ሁለተኛነቷን ለመቆናጠጥ ችላለ
| < Prev | Next > |
|---|


