ድርጅቱ አምስት መርከቦችን መረከቡን ገለፀ

  • PDF

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 12/2005/ዋኢማ/ - የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክ አገልግሎት ድርጅት የሚሰጠውን አገልግሎት ይበልጥ ለማሻሻል በ5 ቢሊየን ብር እያስገነባቸው ካሉት ዘጠኝ መርከቦች መካከል አምስቱን መረከቡን አስታወቀ።

የድርጅቱ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ስራ አስኪያጅ አቶ ኡስማን አሊ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንደገለፁት፤ ድርጅቱ ከተረከባቸው መርከቦች መካከል ሁለቱ  ነዳጅ ጫኝ ሲሆኑ፤ ሶስቱ የደረቅ ጭነት የሚያጓጉዙ መርከቦች ናቸው።

ሁለቱን ነዳጅ ጫኝ መርከቦች ባህርዳር እና አዋሳ የሚል ስያሜ እንደተሰጣቸው ጠቁመው፤ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ጫኝ መርከቦቹን ደግሞ ፊንፊኒ፣ አሶሳና ጋምቤላ የሚል ስያሜ እንደተሰጣቸው ገልፀዋል።

ወደ ሀገር ውስጥ ያልገቡት አራት መርከቦች እስከ ነሐሴ መጨረሻ ድረስ እንደሚገቡ አቶ ኡስማን ተናግረዋል።

የመርከቦቹን ግዢ ከቻይናው ኤግዚም ባንክ በረዥም ጊዜ ሊከፈል በሚችል የ3 ቢሊየን ብር ብድርና 2 ቢሊየን ብር ደግሞ በራሱ ወጪ ማስገንባቱንም ገልፀዋል።

ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት አገልግሎቱን እየሰጠ ያለው በስድስት መርኮች መሆኑን ገልፀው፤ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡትንና የሚገቡትን ሲጨመሩ ያለውን የመርከብ ቁጥር ወደ 15 ከፍ የሚያደርገው ሲሆን የሚሰጠውን አገልግሎትም ከእጥፍ በላይ ያሳድገዋል ሲሉ ገልፀዋል።

እንደ አቶ ኡስማን ገለፃ ድርጅቱ "የመልቲ ሞዳል" ወይም በአንድ ላይ የተለያዩ አገልግሎቶችን በተሟላ መልኩ ለመተግበር የሚያስችል አቅም ለመፍጠር የሀገር ውስጥ ወደብ ተርሚናሎችን የማስተናገድ አቅምን ለማሳደግ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን፣ ቅርንጫፎችንና የሳተላይት ጣቢያዎችን የማስፋፋት ስራ መስራቱንም ተናግራዋል።

ድርጅቱ በጅቡቲ የገቢ እቃዎች የቆይታ ጊዜን ለመቀነስ የተለያዩ የአሰራር ማሻሻያዎችን ያደረገ ሲሆን፤ በወሰደው ተከታታይ የማሻሻያ እርምጃዎች የመልቲሞዳል ኮንቴይነሮች አማካይ በጅቡቲ ቆይታ ጊዜ በመስከረም 2005 ከነበረበት 63 ቀን ወደ 6 ቀን ዝቅ እንዲል አስችሎታል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክ አገልግሎት ድርጅት ባለፈው አመት የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ አክሲዮን ማህበር፣ የባህር ትራንስፖርትና የደረቅ ወደብ አገልግሎት ድርጅትን በአንድ ላይ በማዋሀድ እንደ አዲስ የተቋቋመ መስሪያ ቤት መሆኑ ይታወቃል።

ድርጅቱ ባለፈው አንድ አመት ጊዜ ውስጥም እራሱን የማደራጀት፣ የድርጅቱን የማዋቅር የማዘጋጀትና የሀገሪቱ የወጪና የገቢ እቃዎች አገልግሎት የመስጠት ስራው እንዳይቋረጥ የበኩሉን ድርሻ ሲወጣ የቆየ መስሪያ ቤት መሆኑን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል።

Subscribe to get latest news

Visitors Counter

mod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_counter
mod_vvisit_counterToday23256
mod_vvisit_counterYesterday27004
mod_vvisit_counterThis week123296
mod_vvisit_counterLast week208463
mod_vvisit_counterThis month590084
mod_vvisit_counterLast month1147369
mod_vvisit_counterAll days( since may 28, 2013)14143543

We have: 241 guests, 54 bots online
No: 54.235.16.159
 , 
Today: Aug 21, 2014