በአፍሪካ አንድነት አመሠራረትና አላማ ውይይት ተካሄደ

  • PDF

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 10/2005 (ዋኢማ) - የአፍሪካ ህብረት 50ኛ የወርቅ ኢዮቤልዮ በዓልን ምክንያት   በማድረግ በአመሰራረቱና በዓላማው ዙሪያ   ጥናታዊ ጹሑፍ   ቀርቦ ውይይት ተደረገበት።
በዚሁ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ባዘጋጀው መድረክ    ከተለያዩ የመንግሥት  መሥሪያ ቤቶች  የተውጣጡ ሠራተኞች  ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች  ቢሮው ምክትል ኋላፊ  አቶ  ፀጋዬ  በየነ  ባቀረቡት  ጥናታዊ  ጹሑፍ  እንደገለጹት  የአፍሪካ  ህብረት 50ኛ  አመት  በዓል ፓናአፍሪካኒዝምና የአፍሪካ  ህዳሴ  በሚል  መሪ  ቃል እየተከበረ  እንደሚገኝ    በመጠቆም የአፍሪካ  አንድነት   ድርጅት  ከምሥረታው  አንስቶ   አፍሪካን  ከጭቆናና  ከባርነት ለማውጣት  የተቋቋመ  ድርጅት እንደሆነ   አስረድተዋል።
የአፍሪካ ህብረት በአህጉሪቷ ህዝቦች መካካል የተጠናከረ አንድነትና ትብብር  ለመፍጠርና  ሉአላዊነትን  ለመጠበቅ ዓልሞ  እንደተነሳ   የገለጹት  አቶ  ፀጋዬ    የአህጉሪቷን  ፖለቲካዊ፣  ማህበራዊና  ኢኮኖሚያዊ   ትስስርን   ለማፋጠን እየሰራ ነው  ብለዋል።

የ50ኛ አመት በዓሉን በአዲስ አበባ ከተማ በደመቀ ሁኔታ ለማክበር ከመንግሥት ተቋማት የተውጣጣ ኮሚቴ መቋቋሙን የጠቀሱት አቶ ጸጋዬ    እስካሁን    የ54 ሃገራት መሪዎች፣   ሚኒስትሮች፣   የልዑካን ቡድኖችና   የአለም አቀፍ    ድርጅቶች እንደሚሳተፉ ተረጋግጧል ብለዋል።

በሲቪል  ሰርቪስ  ዩኒቨርስቲ   መምህር  የሆኑት    ዶክተር  መሐመድ  አብዱላሂም     በበኩላቸው የድርጅቱ   አላማ  በአህጉሪቷ   የአንድነትና  የትብብር  መንፈስ  ማጎልበት  እንደሆነ   ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ  ለረጅም  ጊዜ  ነጻነቷን አስጠብቃ  መቆየቷ   ለሌሎች  አፍሪካ  ሃገሮች  የነጻነት   ተምሳሌት  እንድትሆን    እስችሏል  ያሉት   ዶክተር  መሐመድ   አሁንም    በተለያዩ የአፍሪካ   ሃገራት   የሰላም  አስከባሪ    በመላክ  ለአህጉሪቷ   ሰላምና  ፀጥታ  መከበር  ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገች መሆኑን ገልጸዋል።

Visitors Counter

mod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_counter
mod_vvisit_counterToday12608
mod_vvisit_counterYesterday27561
mod_vvisit_counterThis week140209
mod_vvisit_counterLast week208463
mod_vvisit_counterThis month606997
mod_vvisit_counterLast month1147369
mod_vvisit_counterAll days( since may 28, 2013)14160456

We have: 230 guests, 91 bots online
No: 54.87.72.149
 , 
Today: Aug 22, 2014