ባለፈው ዘጠኝ ወር ከወጪ ንግድ ከ2 ነጥብ 2 ቢለየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

  • PDF

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 2/2005 (ዋኢማ) - ኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከወጪ ንግድ ከ2 ነጥብ 2 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷን የንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሚኒስቴሩ የዘጠኝ ወር አፈፃፀም ሪፖርት እንደሚያሳየው የተገኘው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ59 ነጥብ 83 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ብልጫ አሳይቷል።

በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ካስገኙት የውጭ ምንዛሪ ገቢ አኳያ ከፍተኛ ድርሻ ካበረከቱት የወጪ ምርቶች መካከል ቡና (513.87 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር)፣ ወርቅ (432.101 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር)፣ ቅባት እህሎች (314.5 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር)፣ ጫት (198.87 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር)፣ የጥራጥሬ ሰብሎች (169.83 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር)፣ አበባ (134.51 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር)፣ የቁም እንስሳት (130.29 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር) ይገኙበታል።

በገበያ መዳረሻነት ሶማሊያ የ9 ነጥብ 4 በመቶ ድርሻ ስትይዝ ቻይናና ጀርመን የ8 ነጥብ 3 በመቶ እና የ8 ነጥብ 1 በመቶ ድርሻ ይዘዋል።

ሃገሪቱ ወደ ሶማሊያ ከምትልካቸው ምርቶች የቁም እንስሳት፣ ፍራፍሬ፣ አትክልት፣ ጥራጥሬ እና ቅመማ ቅመም ዋና ዋናዎቹ መሆናቸውን ከንግድ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያሳያል።

Subscribe to get latest news

Visitors Counter

mod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_counter
mod_vvisit_counterToday30572
mod_vvisit_counterYesterday36633
mod_vvisit_counterThis week174280
mod_vvisit_counterLast week342815
mod_vvisit_counterThis month777711
mod_vvisit_counterLast month1188964
mod_vvisit_counterAll days( since may 28, 2013)9031803

We have: 181 guests, 39 bots online
No: 54.204.67.26
 , 
Today: Apr 17, 2014