የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ደንበኞች ቁጥር እድገት አሳየ

አዲስ አበባ ሚያዝያ 29/2000 የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን በያዝነው በጀት ግማሽ ዓመት በሁሉም ዘርፎች የሚሰጠውን አገልግሎት የተሻለ ውጤትና እድገት ማሳየቱን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በ2000 በጀት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ውስጥ በሁሉም የቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፎች የተሻለ ጥረትና እንቅስቃሴ በመደረጉ የመደበኛ ቴሌፎን ደንበኞች ወደ 920ሺ 63፣ የሞባይል ደንበኞች ወደ 1 ሚሊዮን 816 ሺ 946፣ የዲያል አፕ ወደ 28 ሺ 880 እንዲሁም የመልቲ ሚዲያ ደንበኞች ወደ 1ሺ 130 ከፍ ማለቱን ከኮርፖሬሽኑ የተገኘ መረጃዎች ያመላክታሉ።

በመሆኑም ኮርፖሬሽኑ በያዝነው በጀት ግማሽ ዓመቱ መጨረሻ ላይ በሰኔ 1999 በጀት ዓመት ከነበረው የመደበኛ ቴሌፎን ደንበኞች በ3.2 በመቶ፣ የሞባይል ደንበኞች 50 በመቶ እና የመልቲ መዲያ ደንበኞች ደግሞ በ9.07 በመቶ እድገት ማሳየቱን ያሳያል።

እንዲሁም በገጠር ቴሌኮም ውስጥ የተገናኙት የገጠር ቀበሌዎች ቁጥር ከ7ሺ389 ወደ 9 ሺ 174 ከፍ በማለቱ የ24 በመቶ እድገት ማስመዝገቡን መረጃዎች ያመላክታሉ።

በተመሳሳይ መልኩ በሰኔ 1999 ከነበረው የኔትዎርክ አቅምም በመደበኛ ቴሌፎን 6.52 በመቶ፤ በሞባይል ቴሌፎን 65 በመቶ ከፍ ማለቱን ከኮርፖሬሽኑ የተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

የ2000 በጀት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የኮርፖሬሽኑ የአገልግሎት ደረጃ ከ1999 በጀት መጨረሻ ጋር በንጽጽር የሚያሳይ ሰንጠረዥ ከዚህ በታች ቀርቧል።

የአገልግሎት/ኔትዎርክ አይነት

 

የኔትወርክ አቅም

የደንበኛ ብዛት

ለውጥ

በኔትወርክ አቅም

በደንበኞች

ሰኔ 1999

ታህሳስ 2000

ሰኔ 1999

ታህሳስ 2000

በቁጥር

%

በቁጥር

%

የመደበኛ ቴሌፎን

1,070,907

1,140,773

890,741

920,063

69,866

6.52

29322

3.2

የሞባይል ቴሌፎን

1,375,000

2,278,516

1,208,498

1,816,946

903,516

65

608,448

       50

የዲያልአኘ ኢንተርኔት

100,000

100,000

31,400

28,880

-

 

(2,600)

(8.28)

የመልቲሚዲያ ደንበኞች

2.5G

 

1,036

1,130

-

 

94

9.07

ስኩልኔት

 

 

625

636

 

 

11

1.76

የገጠር ቴሌኮም ደንበኞች

 

 

7,389

9,174

 

 

1,785

24

ምንጭ፡- የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን