|
ሚያዝያ 22/2000 በሀገራችን እ.ኤ.አ ከ2003-2005 ባሉት
ጊዜያት አንድ ሴት የምትወልዳቸው የልጆች መጠን በአማካኝ 5.4 መሆኑን ከማዕከላዊ
እስታስቲክስ ኤጀንሲ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
ከኤጀንሲው የተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ባለፉት ሦስት ዓመታት
ማለትም እ.ኤ.አ በ2003-2005 በመላ ሀገሪቱ ማለትም በገጠርና በከተማ ያለውን የወሊድ
መጠን ለማወቅ በተደረገው ጥናት መሠረት በአማካኝ አንዲት ሴት 5.4 ልጆች እንደምትወልድ
ያሳያል።
ይሁን እንጂ በሀገረቱ በሚገኙ የገጠር አካባቢዎች የሚወለዱ ህፃናት
ቁጥር በከተሞች አካባቢ ከሚወለዱ የህፃናት ቁጥርና የወሊድ መጠን በጣም ከፍ እንደሚል
መረጃው ይጠቁማል።
በመሆኑም ከአጠቃላይ የሀገሪቱ የወሊድ መጠን ጋር ሲነፃፀር በገጠር
በአማካኝ የአንድ ሴት የወሊድ መጠን 6.0 ሲሆን በከተማ ደግሞ የወሊድ መጠኑ 2.4 ነው።
ይህም የገጠሩ የወሊድ መጠን ከከተማው የወሊድ መጠን ጋር ሲነፃፀር በ 2.5 እንደሚበልጥ
ያሳያል።
በከተማና በገጠር በሚገኙ የወላድ ሴቶች ቁጥር መካከል ሰፊ ልዩነት
መኖሩን የሚያሳየው በተለይ ከ20 እስከ 34 ዕድሜ ክልል ውስጥ በሚገኙ የገጠር ወላድ
ሴቶች መካከል መሆኑን ያሳያል።
ከ2003-2005 እ.ኤ.አ ባሉት ጊዜያት በሀገሪቱ አጠቃላይ
የወሊድ መጠን በእድሜ፣ በከተማና በገጠር በንጽጽር የሚያሳይ ሰንጠረዥ ከዚህ በታች
ቀርቧል።
|
መኖሪያ |
|
እድሜ |
ከተማ |
ገጠር |
አጠቃላይ |
|
ከ15-19 |
35 |
122 |
104 |
|
ከ20-24 |
105 |
260 |
228 |
|
ከ25-29 |
133 |
261 |
241 |
|
ከ30-34 |
101 |
253 |
231 |
|
ከ35-39 |
58 |
178 |
160 |
|
ከ40-44 |
28 |
94 |
84 |
|
ከ45-49 |
14 |
38 |
34 |
|
አጠቃላይ የወሊድ መጠን |
2.4 |
6.0 |
5.4 |
ማስታወሻ፡-
እያንዳንዱ በቁጥር የተጠቀሰው የወሊድ መጠን ከ1000 ወላድ ሴቶች አንጻር ነው
ምንጭ፡-
ማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ |