ከ9 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኘ

 

አዲስ አበባ የካቲት 26/2000 መንግሥት በያዝነው በጀት ግማሽ ዓመት ከታክስና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች፣ ከጉምሩክ ቀረጥና ከሎተሪ ሽያጭ ከ9 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን ከገቢዎች ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ከሚኒስቴር መ/ቤቱ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በ2000 በጀት መጀመሪያ መንፈቅ ዓመት ብር 10 ቢሊዮን 246 ሚሊዮን 36 ሺህ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ ብር 9 ቢሊዮን 729 ሚሊዮን 51 ሺህ ወይም የእቅዱን 94.99 በመቶ መሰብሰቡን ጠቁሟል።

በመንፈቅ ዓመቱ የተሰበሰበው ይኼው ገቢ ከ1999 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ክንውን ጋር ሲነፃፀር የብር 2 ቢሊዮን 826 ሚሊዮን 4 ሺህ ወይም 40.94 በመቶ እድገት ማሳየቱ መረጃው ያሳያል።

ከተሰበሰበው አጠቃላይ ገቢ ውስጥ የፌዴራል አገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን 44.18 በመቶ፣ የጉምሩክ ባለሥልጣን 55.69 በመቶ እና የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር 0.13 በመቶ ድርሻ እንዳላቸው መረጃው ያሳያል።

በበጀት ዓመቱ መንፈቅ በሦስቱ መስሪያ ቤቶች የተሰበሰበው የመንግሥት ገቢ ከ1999 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ገቢ በንጽጽር ቀጥሎ ባለው ሠንጠረዥ ቀርቧል።

 

በሚሊዮን ብር

ተራራ ቁጥር

የገቢ ሰብሳቢ መ/ቤቱ ስም

የዓመቱ ዕቅድ

የ2000 የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት

የ1999 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት  ክንውን

ከ1999 የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት  ክንውን ጋር ሲነፃፀር

ከዓመቱ ዕቅድ ጋር ሲነፃፀር

ዕቅድ

ክንውን

በብር

በብር

በብር

በመቶኛ

በብር

በመቶኛ

በመቶኛ

1

2

3

4=.3/2*%

5

6=(3-5)/5*%

7=(3/1*%

1

የፌዴራራል አገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን

7510.70

4020.49

4298.53

106.92

3119.07

37.81

57.23

2

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለሥልጣን

12864.75

6209.62

5418.30

87.26

3774.20

43.56

42.12

3

የብሔራራዊ ሎተሪ አስተዳደር

28.28

12.25

12.68

103.51

10.20

24.31

44.84

 

ጠቅላላ የፌዴራራል የመንግሥት ገቢ ድምር

20403.73

10242.36

9729.51

94.99

6903.47

40.94

47.68

ምንጭ፡- የገቢዎች ሚኒስቴር