የፌዴራል መንግሥት ከ19 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ አደረገ

አዲስ አበባ መጋቢት 16/2000 የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት በያዝነው በጀት ግማሽ ዓመት ለመደበኛ፣ ለካፒታልና ለክልሎች የበጀት ድጋፍ ከ17 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ማድረጉን መረጃዎች ያመላክታሉ።

ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት በበጀት ዓመቱ ለመደበኛ፣ ካፒታልና ለክልሎች የበጀት ድጋፍ ከታቀደው ብር 37 ቢሊዮን 784 ሚሊዮን ውስጥ 17 ቢሊዮን 352 ሚሊዮን 900 ሺህ ወይም የእቅዱን 46 በመቶ ያህሉን ማከናወኑን ያሳያሉ።

በበጀት ዓመቱ ግማሽ ዓመት ለተለያዩ ተግባራት ማስፈፀሚያ ወጪ የተደረገው ገንዘብ መጠን ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ወጪ መጠን ጋር ሲነፃፀር የብር 1 ቢሊዮን 206 ሚሊዮን 700 ሺህ ወይም 31 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን መረጃዎች ጠቁሟል።

ከአጠቃላይ ወጪ ውስጥ ለመደበኛ ወጪዎች የተከፈለው ብር 4 ቢሊዮን 88 ሚሊዮን 900 ሺህ የጠቅላላ ወጪውን 24 በመቶ የሚሸፍን ሲሆን፣ ለካፒታል ወጪዎች የተከፈለው ብር 6 ቢለዮን 766 ሚሊዮን ከጠቅላላው ወጪ 39 በመቶ ሲሆን በሌላ በኩል ለክልሎች የተላለፈ በጀት ድጋፍ ብር 6 ቢሊዮን 498 ሚሊዮን ሲሆን ይህም የጠቅላላ ወጪውን 37 በመቶ ድርሻ እንዳለው መረጃዎች ያመላክታሉ።

የ2000 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ግማሽ የፌዴራል መንግሥት የመደበኛና የካፒታል ወጪ አፈፃፀም ከ1999 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አፈፃፀም ጋር በንፅፅር ሰንጠረዥ ከዚህ በታች ቀርቧል።

በሚሊዮን ብር

 

ዝርዝር

የዓመቱ እቅድ

የ 6 ወር ክንውን

ልዩነት ካለፈው ዓመት

የ 6 ወሩ አፈፃፀም ከዓመቱ እቅድ

2000

1999

በብር

በመቶኛ

በመቶኛ

ጠቅላላ ወጪ

37783

17353

13222

4131.3

31.2

45.9

መደበኛ ወጪ

10019

4088.9

2882.1

1206.8

41.9

40.8

   አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት

4772

2604.5

1654.8

949.7

57.4

54.6

የኢኮኖሚ አገልግሎት

589

186.3

167.4

18.9

11.3

31.6

ማኅበራዊ አገልግሎት

1630

768.0

519.2

248.8

47.9

47.1

ልዩ ል ወጪዎች

3027

530.1

540.7

-10.6

-2.0

17.5

የካፒታል ወጪ

14209

6765.5

5750.0

1015.5

17.7

47.6

የኢኮኖሚ ልማት

9457

4627.3

4611.3

16.0

0.3

48.9

ማኅበራዊ ልማት

3012

1228.6

1021.7

206.9

20.3

40.8

ጠቅላላ ልማት

1740

909.6

117.0

792.6

677.4

52.3

የክልሎች ድጋፍ

13555

6498.4

4589.4

1909.0

41.6

47.9

ከካፒታል ወጪ ውስጥ

 

 

 

 

 

 

የአገር ውስጥ ምንጭ

11506

5916.2

4956.3

959.9

19.4

51.4

የውጭ አገር ብድር

2703

849.4

793.7

55.7

7.0

31.4

ምንጭ፡- ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር