|
ከወጪ ንግድ ከ533 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ |
||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||
|
አዲስ አበባ መጋቢት 3/2000 በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ውስጥ ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች ከ533 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ የተገኘ መሆኑን ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል። መረጃዎቹ እንደሚያመላክቱት በ2000 በጀት የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት ወደ ውጪ ከተላኩ የተለያዩ የሀገር ውስጥ ምርቶች 533 ሚሊዮን 600 ሺ ዶላር የውጭ ምንዛሬ የተገኘ ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አፈፃፀም ጋር ሲነፃፀር በ98 ሚሊዮን 700 ሺህ ዶላር ወይም 22.7 በመቶ ብልጫ እንዳለው ይጠቁማል። ወደ ውጭ ከተላኩት ምርቶች ለተገኘው ገቢ ከፍተኛውን ድርሻ የያዘው ቡና ሲሆን ከቡና ቀጥሎ ያለውን ከፍተኛ መጠን የያዙት የጥራጥሬ፣ የቅባት እህልና የቅመማ ቅመም ምርቶች መሆናቸውን መረጃው ያሳያል። በግማሽ ዓመቱ ውስጥ ከቡና የወጪ ምርት የተገኘው ገቢ 144 ሚሊዮን 900 ሺህ ዶላር ወይም ከጠቅላላው ገቢ 27 በመቶ ሲሸፍን፣ ከጥራጥሬ፣ የቅባት እህሎችና ቅመማ ቅመም የውጪ ምርቶች የተገኘው 126 ሚሊዮን 800 ሺህ ዶላር ወይም ከጠቅላላው ወጪ ምርት ዋጋ 23.8 በመቶ መሸፈኑን እና ቀሪው ደግሞ ከተለያዩ የወጪ ምርት ሽያጭ የተገኘ መሆኑን መረጃው ያመላክታል። የ2000 በጀት የስድስት ወራት የወጪ ንግድ አፈፃፀም ከ1999 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር በንጽጽር የሚያሳይ ሰንጠረዥ ከዚህ በታች ቀርቧል። በሚሊዮን ዶላር
ምንጭ፡- ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር |
||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||
|
|
|
|