የማዳበሪያና የምርጥ ዘር አቅርቦትና ሥርጭት እድገት አሳየ

አዲስ አበባ ጥር 21/2000 በሀገሪቱ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሚደረገውን ብሔራዊ ጥረት ለማገዝ እንዲቻል ለአርሶ አደሩ የሚያስፈልጉት የማዳበሪያና የምርጥ ዘር አቅርቦትና ሥርጭት እድገት ማሳየቱን መረጃዎች ያመላክታሉ።

ከማስታወቂያ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የማዳበርያ ሥርጭት በ1994 በጀት ዓመት ከነበረበት 232ሺ 270 ቶን በ1999 በጀት ዓመት ወደ 388ሺ 141 ቶን ሲደርስ የምርጥ ዘር አቅርቦት ደግሞ በ1993/94 ከነበረበት 36ሺ244 ኩንታል በ1999 በጀት ዓመት ወደ 154ሺ 157 ኩንታል እድገት አሳይቷል።

በአገሪቱ የማዳበሪያ ሥርጭት ሆነ የምርጥ ዘር አቅርቦት እድገት ሊያሳይ የቻለው መንግሥት የማዳበሪያ ፖሊሲ አውጥቶ ፖሊሲውን በተግባር ላይ ለማዋል በመቻሉ መሆኑን መረጃው ያሳያል

በተጨማሪ ለረዥም ዓመታት በአንድ መንግሥታዊ ድርጅት ብቻ ተይዞ የቆየው የማዳበሪያ የንግድ ሥራ በአሁኑ ወቅት በአንድ የመንግሥት፣በሁለት የግልና በ11 የኅብረት ሥራ ዩኒኖች በጠቅላላው በ14 በማዳበሪያ ንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች  እንዲከፋፈል መደረጉ ለአቅርቦቱ መሻሻል አስተዋጸኦ ማድረጉን መረጃው ያሳያል።

በየዓመቱ የሚሸጠው ጠቅላላ የማዳበሪያ መጠን ውስጥ ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነው ጥቅም ላይ የሚውለው ከፍተኛ የማዳበሪያ ተጠቃሚ በሆኑት በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በትግራይና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መሆኑን መረጃው ጠቅሷል።

በተጨማሪ መንግሥት የግብርናን ምርት ለማሳደግ የኢትዮጵያ የምርጥ ዘር ድርጅትን አሰራር በማሻሻል ምርጥ ዘርና ሌሎች ግብዓቶች ከተሻሻለ የግብርና አሰራር ጋር አቀናጅቶ በአርሶ አደሩ ዘንድ እንዲታወቁ ከማድረግ ባሻገር የግል የዘር አምራች ኩባንያዎች ለማቋቋም ሁኔታዎች ማመቻቸቱን መረጃዎች ያመላክታሉ።

እንዲሁም በአንድ የግል ኩባንያ ብቻ ሲካሄድ የነበረው የዘር ማባዛትና የማሰራጨት ሥራ በአሁኑ ወቅት ከ16 በላይ በሆኑ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የገበሬው የምርጥ ዘር ፍላጎት ከዓመት ወደ ዓመት እየጨመረ በመምጣቱ ከተጠቀሱት ምርጥ ዘር አምራቾች ድርጅቶች በተጨማሪ ዘር በክልሎች ገበሬ ማሳ ላይ በስፋት እየተባዛ ሥራ ላይ የሚውልበት ሁኔታ መፈጠሩን ከሚኒስቴር መ/ቤቱ የተገኘው መረጃ ያረጋግጣል።

የማዳበሪያ እና የምርጥ ዘር አቅርቦትና ሥርጭት በተመለከተ ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን ሁለት ሠንጠረዥ ይመልከቱ።

ሠንጠረዥ 1

                  የማዳበሪያ አቅርቦት በሜትሪክ ቶን / 1994-1999 ዓ.ም/

ዘመን

           ዳፕ

ዩሪያ

ጠቅላላ

1994

155,941

76,329

232,270

1995

157,955

106,394

264,349

1996

210,838

112,101

322,939

1997

224,819

121,735

346,554

1998

251,000

125,000

376,000

1999

259,020

129,121

388,141

 

ሠንጠረዥ 2

               የምርጥ ዘር ሥርጭት በሰብል ዓይነትና ሽያጭ በኩንታል

ዓ.ም

ስንዴ

በቆሎ

ገብስ

ማሽላ

ጤፍ

ቦሎቄ

ሌሎች

ድምር

1993/94

7,934

25,726

533

63

600

884

502

36,244

1994/95

-

-

-

-

-

-

-

166,119

1995/96

140,914

68,566

1,628

0.3

1,626

2,376

1,573

216,683

1996/97

68,416

66,430

3,955

443

2,233

2,486

15,180

159,150

1997/98

132,312

65,512

10,023

139

3,527

4369

9428

225,310

1998/99

76,600

54,747

6,354

278

5,816

2,237

9,123

154,157

ምንጭ፡- የማስታወቂያ ሚኒስቴር