|
የኢትዮጵያ ቴሌኮሚኒኬሽን ኮርፖሬሽን አገልግሎት እድገት አሳየ |
|||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||
|
አዲስ አበባ የካቲት/ 2000 የኢትዮጵያ ቴሌኮሚኒኬሽን ኮርፖሬሽን በሀገሪቱ በሁሉም የቴሌኮሚኒኬሽን ዘርፎች የሚሰጠው የአገልግሎት ደረጃ መሻሻልና እድገት ማሳየቱን መረጃዎች ያመላክታሉ። ከኮርፖሬሽኑ የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት በሁሉም የቴሌኮሚኒኬሽን ዘርፎች ከፍተኛ ውጤት ለማስመዝገብ በተደረገው እንቅስቃሴ መሰረት በ1999 በጀት አመት መጨረሻ ላይ የመደበኛ ቴሌፎን ደንበኞች 31ሺ741፣ የሞባይል ደንበኞች 1ሚሊዮን 208ሺ489፣ የዲያል አፕ ኢንተርኔት ደንበኞች 31ሺ 400 እንዲሁም የመልቲ ሚዲያ ደንበኞች ቁጥር 1ሺ 36 የደረሰ መሆኑን ያሳያል። በዚህ መሰረት የኮርፖሬሽኑ የ1999 በጀት ዓመት የዕቅድ ክንውን ከ1998 በጀት ዓመት ክንውን ጋር ሲነጻጸር የመደበኛ ቴሌፎን ደንበኞች በ20 በመቶ፣የሞባይል ደንበኞች በ40 በመቶ፣ የኢንተርኔት ደንበኞች ደግሞ በ38 በመቶ ብልጫ ያለው መሆኑን መረጃዎቹ ያመላክታሉ። ባለፉት አምስት አመታት ውስጥ የመደበኛ ቴሌፎን እና የሞባይል አገልግሎት እንዲሁም የደንበኞች ቁጥር እድገት እያሳየ ቢሆንም የኔትወርኩ እድገት ከደንበኞቹ እድገት ጋር ያልተጣጣመ በመሆኑ በቀጣይነት ሰፊ የማስፋፋት ሥራ መከናወን እንዳለበት መረጃዎቹ ይጠቁማሉ። የ1999 በጀት ዓመት የኮርፖሬሽኑ የአገልግሎት ደረጃና ክንውን ከ1998 በጀት ዓመት ክንውን ንጽጽር ቀጥሎ ባለው ሰንጠረዥ ቀርቧል።
ምንጭ:- የኢትዮጵያ ቴሌኮሚኒኬሽን ኮርፖሬሽን |
|||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||
|
|
|
|