|
የውጭ ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ቁጥር እድገት እሳየ |
||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||
|
አዲስ አበባ የካቲት 12/2000 የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ በ2000 በጀት ዓመት የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት ውስጥ የኢንቨስትመንት ፈቃድ የሰጣቸው ፕሮጀክቶች በካፒታል መጠንና በሚፈጥሩት የሥራ እድል እድገት ማሳየቱን መረጃዎች ያመላክታሉ። ከኤጀንሲው የተገኘ መረጃ እንደሚያመላክተው ከሐምሌ 1/1999 እስከ ታህሳስ 30/2000 ባሉት ጊዜያት ውስጥ በአጠቃላይ በሀገሪቱ በተለያዩ ክልሎች ከተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፍ ለሚሳተፍ 915 ፕሮጀክቶች ፈቃድ ተሰጥቷል። ኤጀንሲው የኢንቨስትመንት ፈቃድ የተሰጣቸው 915 ፕሮጀክቶች በ30.283 ቢሊዮን ብር ካፒታል መጠን የሚንቀሳቀሱ ሲሆን ይህም ለ157,102 የሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የሥራ እድል የፈጠሩ መሆኑን ጠቁሟል። በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት ውስጥ ኤጀንሲው የኢንቨስትመንት ፈቃድ ከሰጣቸው 915 ፕሮጀክቶች መካከል 847 የውጭ ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ሲሆኑ የውጭ ፕሮጀክቶች ድርሻ በቁጥር 92.6 በመቶ፣ በካፒታል መጠን ደግሞ 89.7 እንደሆነ መረጃው ያመላክታል። እንዲሁም በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያው መንፈቀ ዓመት ኤጀንሲው ፈቃድ የሰጣቸው የውጭ ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች በ1999 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ፈቃድ ከሰጣቸው የውጭ ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ጋር ሲነፃፀር በቁጥር 326 ፕሮጀክቶች ማለትም 62.6 በመቶ ከፍ ያለ መሆኑ ከኤጀንሲው የተገኘ መረጃ ያስረዳል። በአጠቃላይ የኢንቨስትመንት ፈቃድ የተሰጣቸው ፕሮጀክቶች በካፒታል መጠንና በሚፈጥሩት ቋሚ የሥራ ዕድል ብዛት በየክፍለ ኢኮኖሚው እና የፕሮጀክቶቹ ክልላዊ ሥርጭት በሚቀጥሉት ሁለት ሰንጠረዦች ቀርቧል። ሠንጠረዥ 1፡- የኢንቨስትመንት ፈቃድ የተሰጣቸው ፕሮጀክቶች ክፍለ ኢኮኖሚ ያዊ ስርጭት ፣ የካፒታል መጠንና የሚፈጥሩት ቋሚ የሥራ ዕድል ብዛት ግምት (ሐምሌ 1/1999 - ታህሣሥ 30/2000)
ሠንጠረዥ 2፡-የኢንቨስትመንት ፈቃድ የተሰጣቸው ፕሮጀክቶች ክልላዊ ስርጭት በካፒታል መጠን (ሐምሌ 1/1999 - ታህሣሥ 30/2000)
ምንጭ፡- የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ
|
||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||
|
|
|
|