|
የንግድ መርከብ አክሲዮን ማህበር ከ1 ሚሊዮን ቶን በላይ እቃዎች አጓጓዘ |
|||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||
|
አዲስ አበባ ሚያዚያ 15/2000 የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ አክሲዮን ማህበር በ2000 ግማሽ ዓመት በወጪና ገቢ እቃዎች ከ1 ሚሊዮን ቶን በላይ እቃዎች መጓጓዙን መረጃው ጠቋሟል። ከኩባንያው የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በበጀት ግማሽ ዓመቱ ውስጥ በወጪ እቃ፣ በገቢ እቃ እንዲሁም በውጭ ሀገር ወደቦች መካከል የተጓጓዘውን ጨምሮ 860 ሺ 677 ቶን ዕቃ ለማጓጓዝ አቅዶ 1 ሚሊዮን 203 ሺህ 139 ቶን ማለትም የእቅዱ 140 በመቶ ማከናወኑን ያሳያል። ኩባንያው በበጀት ግማሽ ዓመቱ ውስጥ ለማጓጓዝ የቻለው እቃ ካለፈው ዓመት ተመሣሣይ ወቅት ክንውን ጋር ሲነፃፀር የ66 በመቶ ብልጫ እንዳለው ያሳያል። ክንውኑ ሊበልጥ የቻለው የሃገሪቷን የውጭ ንግድ ከመጨመሩ ጋር በተያያዘ ኩባንያው በራሱ መርከቦች እንዲሁም በተጠናከረ መልኩ የኪራይ የመርከብ ድርጅቶችን መርከቦች የጭነት ቦታ ተከራይቶ በመስራቱ መሆኑን መረጃው ያስረዳል። በግማሽ ዓመቱ ውስጥ ከተጓጓዘው እቃ 393 ሺ 267 ቶን ወይም 33 በመቶ በኩባንያው መርከቦች ሲሆን 809 ሺ 872 ቶን ወይም 67 በመቶ ደግሞ በኪራይ መርከቦች መሆኑን ጠቋሟል። በግማሽ ዓመቱ ውስጥ ከተጓጓዘው እቃ መጠን ውስጥ 48 በመቶ ያህሉ በኮንቴይነር ታሽጐ የተጓጓዘ ሲሆን 7 በመቶ በመኪና ጭነት እንዲሁም 45 በመቶ ጥቅል ዕቃዎች ጭነት መሆኑን ከኩባንያው የተገኘው መረጃ ያመላክታል። ¾ኩባንያው የ2000 ግማሽ ¯Sƒ ¾›ÑMÓKAƒ °pÉ ›ðíìU በሚቀጥለው ሰንጠረዥ ቀርቧል u„”
| |||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||