|
4 ቢሊዮን ብር በላይ በብድርና በእርዳታ ተገኘ |
||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||
|
አዲስ አበባ ሚያዝያ 8/2000:በሀገሪቱ በያዝነው በጀት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ውስጥ ከተለያዩ የውጭ ሀገር ለጋሽ መንግሥታትና ድርጅቶች ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ በእርዳታና በብድር አማካኝነት እንደተገኘ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ይጠቁማል። መረጃው እንደሚያስረዳው የተገኘው ብር 4 ቢሊዮን 237 ሚሊዮን 320 ሺህ ሲሆን ከዚሁ ውስጥ ብር 3 ቢሊዮን 195 ሚሊዮን 600 ሺህ በብድር፣ ብር 1 ቢሊዮን 41 ሚሊዮን 720 ሺህ የሚሆነው ደግሞ በእርዳታ አማካኝነት እንደሆነ ያመላክታል። ከዚሁ ውስጥ ከመልቲላተራል ለጋሽና አበዳሪ ድርጅቶች የተገኘው ብር 2 ቢሊዮን 865 ሚሊዮን 170 ሺህ ውስጥ ብር 2 ቢሊዮን 97 ሚሊዮን 600 ሺህ የተገኘው በብድር ሲሆን ቀሪው ብር 767 ሚሊዮን 570 ሺህ ደግሞ በእርዳታ መልክ መሆኑን መረጃው ያሳያል። እንዲሁም ከባይላተራል ወይም ከመንግሥታት ትብብር አማካኝነት የተገኘው ብር 1 ቢሊዮን 372 ሚሊዮን 150 ሺህ ሲሆን ከዚሁ ውስጥ 1 ቢሊዮን 98 ሚሊዮን የሚሆነው በብድር ቀሪው ብር 274 ሚሊዮን 150 ሺህ ደግሞ በእርዳታ አማካኝነት መሆኑን ከሚኒስቴር መ/ቤቱ የተገኘ መረጃ ያስረዳል። በ2000 በጀት ዓመት በመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ውስጥ አዲስ የተገኘ ብድር እና እርዳታ in (‘000)
| ||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||