|
የጤና ተቋማትና የባለሙያዎች ቁጥር እድገት አሳየ |
||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||
|
አዲስ አበባ ሚያዝያ 2/2000 በአገራችን ከ1995 እስከ 1999 ዓ.ም ባሉት ጊዚያት ውስጥ የጤና አገልግሎት መስጫ ተቋማትና የጤና ባለሙያዎች ቁጥር እድገት ማሳየቱን መረጃዎች ያመላክታሉ። ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው በ1995 ዓ.ም 119 የነበረው የመንግሥት ሆስፒታሎች ቁጥር በ1999 ዓ.ም ወደ 143 ማደጉን ያሳያል። እንዲሁም በ1995 ዓ.ም በትርፍ ሥራ የተሰማሩ የግል ጤና ቁጥር 1229 የነበሩ ሲሆን በ1999 ዓ.ም ወደ 1756 ማደጉን መረጃው ያመላክታል። በህክምና ባለሙያዎች በኩል ደግሞ በ1995 ዓ.ም 2032 የነበረው የሀኪሞች ቁጥር በ1999 ዓ.ም 1806 መድረሱን እንዲሁም በ1996 ዓ.ም 2737 የነበረው የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ቁጥር በ1999 ዓ.ም ወደ 17,653 ከፍ ማለቱን መረጃው ጠቁሟል። ከ1995 እስከ 1999 ዓ.ም የጤና አገልግሎት መስጫ ተቋማትና የባለሙያዎች ቁጥር እድገት የሚያሳይ ሰንጠረዥ ከዚህ በታች ቀርቧል።
|