|
ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከለጋሾች ድርጅቶች ድጋፍ ተሰጠ |
||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||
|
አዲስ አበባ መጋቢት 23/2000 በያዝነው በጀት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ውስጥ ከተለያዩ ለጋሽ ድርጅቶች ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚሆን ድጋፍ ለተለያዩ የእርዳታ አስፈፃሚ ድርጅቶች መስጠቱን መረጃዎች ያመላክታሉ። ከአደጋ መከላከያና ዝግጁነት ኤጀንሲ የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ከሐምሌ 1 ቀን 1999 እስከ 2000 ታህሳስ ባለው ስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ከተለያዩ ለጋሽ ድርጅቶች ምግብ ነክ ላልሆኑ አገልግሎቶች የሚውል 6 ሚሊዮን 22 ሺህ 702 ዶላር በሀገሪቱ ለሚንቀሳቀሱ የተለያዩ የእርዳታ አስፈፃሚ ድርጅቶች ተሰጥቷል። ከለጋሽ ሀገሮችና ድርጅቶች በአጠቃላይ ከተለገሰው ድጋፍ 2 ሚሊዮን 717 ሺህ 302 ዶላር ለውሃ አቅርቦት፣ 2 ሚሊዮን 759 ሺህ 505 ዶላር ለጤና እንዲሁም 545 ሺህ 895 ዶላር የሚሆነው ደግሞ እርሻ ግብዓት መሆኑን መረጃዎቹ ይጠቁማሉ። በዚህ የልገሳ ተግባር ላይ የተሳተፉ ድርጅቶች እንደ USAID/OFDA,HRF, USTHEMATIC በአገር ደረጃ SPAIN ሲሆኑ እርዳታውን ተቀብለው የሚያስፈጽሙ ድርጅቶችም እንደ UNICEF, CHF, GAA, SC/US, GOAL, IMC CONCERN መሆናቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ። የለጋሽ ድርጅቶች፣ የድጋፍ መጠንና ሴክተር እንዲሁም የአስፈፃሚ ድርጅቶች ዝርዝር የሚያሳይ ሰንጠረዥ ከዚህ በታች ቀርቧል።
ምንጭ፡- ከአደጋ መከላከያና ዝግጁነት ኤጀንሲ |
||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||
|
|
|
|