|
ሚያዝያ 7 ቀን፤ 2000 ዓ/ም
እሁድ ሚያዝያ 5 ቀን በኢትዮጵያ ሶስተኛው የአካባቢና የማሟያ ምርጫ ተካሂዷል፡፡ ምርጫው
ከ1997 ድህረ ምርጫ ቀውስ በኋላ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ወደኋላ ተመልሷል የሚል ጥርጣሬ
የነበራቸውን ወገኖች ሁሉ ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ እንዳልተቀለበሰ ይልቁንም በጥንካሬ ወደፊት
እየተራመደ እንደሆነ ማረጋገጫ በመሆን ግምታቸውን ስህተት አድርጎታል፡፡
ምርጫው በተቃዋሚዎች ጥያቄ ሁለት ጊዜ ተራዝሞ ነው ባለፈው እሑድ የተካሄደው ይህም
በአገራችን የተቃዋሚዎችን ድምና ጥያቄ ረግጦ የሚራመድ መንግስት እንደሌለ አረጋግጧል፡፡
አዲሱ የምርጫ ቦርድ በገዢና በተቃዋሚ ፓርቲዎች የጋራ ስምምነት ከተመሰረተ በኋላ በአጭር
ጊዜ ውስጥ የተሳካ ምርጫ ሊያካሂድ መቻሉ ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ተቋሞች ከፍተኛ ድል ነው፡፡
በምርጫው ለመሳተፍ 27 ሚሊዮን ህዝብ ተመዝግቧል፡፡ ይህም ካለፈው በአንድ ሚለዮን ብልጫ
አለው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ዴሞክራሲን የፍላጎቱ ማስፈፀሚያና ህጋዊ የትግል መሣሪያ
ለማድረጉ ተጨማሪ ማረጋገጫ ነበር፡፡ ዘግይቶ የጀመረም ቢሆን ሁሉም ፓርቲዎች በድምር
ከ140 ያላነሰ የአየር ሰዓት አግኝተው አላማቸውን ለህዝብ አስተዋውቀዋል፡፡ በሬድዮና
በቴሌቪዥን የተለመደው የፓርቲ ክርክር ተካሂዷል፡፡ ክርክሩ እንደ 97 መረን የለቀቀ
ባይሆንም ፓርቲዎች አላማቸውን ለማስተዋወቅ የቻሉበት መሆኑ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ እንደገና
ወደፊት መራመዱን አመልካች ነበር፡፡
የመጨረሻው የምርጫ ዴሞክራሲያዊነት ማረጋገጫ ከ90% በላይ
m‰+
ድምፁን መስጠቱ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ እንኳን
k1,028,000
m‰+
800 ሺ ያህል ድምፁን ሰጥቷል፡፡ ይህ አሃዝ በ97 ዓ.ም.
በአዲስ ከተማ ድም ከሰጠው
m‰+
በጥቂት ሺህ ሰዎች ብቻ ያነሰ ነው፡፡ በአሁኑ ምርጫ በአዲስ አበባ ከተማ ለመምረጥ
ከተመዘገበውም 80% ያህል ህዝብ ድምፁን መስጠቱን ያሳያል፡፡ አገሬ ኢትዮጵያ በዚህ
ልትኮራ ይገባታል፡፡ የአዲስ አበባ ህዝብ ከዚያ ሁሉ ድህረ ምርጫ ትርምስ በኋላ በምርጫ
ላይ እምነት አላጣም፡፡ ድምፁን በነቂስ ወጥቶ ለመስጠት መቻሉ ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ ይበልጥ
ሥር እየሰደደ እንደሆነ አመላካች ነው፡፡
በዚህ ምርጫ ጥቂት ጤናማ ያልሆኑ ዝንባሌዎች የታዩት በህብረት መውጣትና ከምርጫው መጠናቀቅ
በኋላ በለስላሳ /የሲቪል/ አላማዎች ላይ በተካሄደው ፍንዳታ ናቸው፡፡ ህብረት ምርጫው
እሁድ ሊካሄድ አርብ እለት ቀኑ ለሦስተኛ ጊዜ ይራዘም ብሎ ጥያቄ አቀረበ፡፡ ምክንያቱ
ምንም ይሁን ምን ምርጫ እሁድ ሊካሄድ አርብ እለት የማራዘሚያ ጥያቄ ማቅረብ ፈሞ ጤናማ
ጥያቄ አልነበረም፡፡ ህብረት ጤናማ ያልሆነ ጥያቄ ይዞ ቀርቦ ተገቢው ምላሽ አልተሰጠኝም
ብሎ አቋርጦ መውጣትን መርጧል፡፡ ይህስ በፓርቲው በኩል የታየ የተሳሳተ እርምጃ እንጃ ሌላ
ምን ሊባል ኑሯል፡፡ ሌሎቹ ፓርቲዎች ግን እስከመጨረሻው ተሳትፈዋል፡፡ ያገኙት ውጤት ምንም
ይሁን አኩርተውናል፡፡ ለዴሞክራሲ መጎልበት ገንቢ ሚና መጫወት ይሏልም ይኸው ነው፡፡
በሲቪል አላማዎች ላይ የሽብር ጥቃት የሰነዘሩት እነማን እንደሆኑ በተጣራ መረጃ ላይ
ተመስርቶ ለመናገር ጊዜው ገና ቢሆንም በዴሞክራሲ አምነው የተሳተፉት ተቃዋሚ ፓርቲዎች
እንዳልሆኑ ለመገመት አይከብድም፡፡ የኢትዮጵያን በዴሞክራሲና በልማት ጎዳና መገስገስ
የማይወዱት ሻዕቢያና ግብረአበሮቹ እንደሆኑ ግን ለመገመት ጠንቋይ መቀለብ አይጠይቅም፡፡
ሻዕቢያና ኦነግ ምናልባትም ኦብነግ ዴሞክራሲው ርቆ በመሄዱ ተስፋ ቆርጠው የወሰዱት ህዝብን
የማስፈራራትና ገታ የማበላሸት ርምጃ ሊሆን ይችላል፡፡ ሽብር ፈጠራ ተስፋ የቆረጡ ሰዎች
ስልት ነው፡፡ ተስፋ ያላቸው በምርጫ ሲሳተፉ ተስፋ የለሾቹ ቦንብ በማጥመድ ቢሳተፉ
አይገርምም፡፡
በመጨረሻ አዲሱ የምርጫ ቦርድ በኢትዮጵያ የምርጫ ህግ መሠረት ቀልጣፋ
/Efficient/
ምርጫ በማካሄዱ ሊመሰገን ይገባዋል፡፡ የመምረጫ ጣቢያዎችን ቁጥር በእጥፍ ጨምሮ የአገሬው
ሰው በፀሃይ ሳይንቃቃ በጊዜ መርጦ ወደቤቱ እንዲሄድ ለማድረግ በመቻሉ በአገራችን ታሪክ
በጣም ቀልጣፋውንና አብዛኛው
m‰+
የተሳተፈበትን ምርጫ ለማካሄድ አስችሎናል፡፡
ምሥጋና ለምርጫ ቦርድ! |