|
HR- 2003” በኢትዮጵያ §Y የተቀነባበረ œ¤‰ |
| አንድነት መኩሪያ (ዋኢማ)
_NTM ቢሆን ሀገራችን ኢትዮጵያ ነፃነቷን አስ«BÝ ሳትደፈር መቆየቷ እውነት ቢሆንም፣ የራሳቸውን ሀገር ሉዓላዊነት አሣልፈው የሰጡና ለግል ጥቅማቸው በመቆም k«§T UR ywgnù ÆNÄ ወገኖቻችን አልነበሩም ማለት አይቻልም፡፡ ይህንን የቅርቡንም የሩቁንም ታሪክ ቢያገላብጡ የሚያገኙት ሀቅ ነው፡፡ አሁንም በአሜሪካን ኮንግረሥ አባል ዶናልድ ፔይን ጠንሳሽነት ከፀደቀው HR- 2003 ረቂቅ-ህግ ጋር በተያያዘ በአካል ምስክርነት የሰጡና በአቋማቸው የደገፉ በህግ ጥላ ተከልለው የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች (ቅንጅት፣ ኦፌዴን) መንግሥትን ለመጣል የሚንቀሳቀሱ ቡድኖችና (ኦነግ ፣ ኦን.ኤን.ኤልኤፍ) አሸባሪ መንግሥት (ኤርትራ) በይፋ ፀረ-ኢትዮጵያ አቋማቸውን ደግመው አንፀባርቀዋል፡፡ እነዚህን ወገኖች ለየት የሚያደርጋቸው አሁን ከተያያዝነው ፈጣን የልማት እንቅስቃሴ በተቃራኒው መቆማቸው ብቻ አይደለም፡፡ አዲሱ ሚሊኒየም ለሀገራችን ታላቅ ተስፋንና መነሣሣትን ከዳር ዳር እንዲቀጣጠል ባደረገበት ወቅት በተፃራሪ ወገን መቆማቸው እና ህዝቦቻችን ከወትሮው በተለየ ፍፁም አንድነት በአንድ ድም ሥለ ሀገራችን ህዳሴ ሲዘምሩ የነሱ ቅኝት ሌላ መሆኑ እንጂ! ዶናልድ ፔይን ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልሥ ይህ ረቂቅ ህግ በሰኔቱ ፀድቆ በፕሬዚዳንቱ ተፈርሞ ህግ ሲሆን፣ በምሥራቅ አፍሪካ ሰላምና ፀጥታን ለማስፈን ይረዳል፡፡ ማለታቸው የሚታወስ ነው፡፡ ከዚህ አነጋገራቸው ስለ ዶናልድ ፔይን አንዳንድ ነገሮችን ማለት ይቻላል፡፡ ሰውየው አፍሪካ-x»¶µêE እንጂ አፍሪካዊ አይደሉም፡፡ አፍሪካን አያውቋትም፡፡ የአፍሪካን ፖለቲካዊ ቀውሥ፣ ማህበራዊ ሣንካዎችና፣ ወታደራዊ ግጭቶችን ዋሽንግተን ዲሲ tqMጦ b¸ወጡ ማዕቀቦችና ችሮታዎች መፍታት አለመቻሉን በትክክል የተገነዘቡ አይመሥሉም፡፡ ከአፍሪካ ዋና ዋና ዞኖች መካከል አንዱ የሆነውን ምሥራቅ አፍሪካን በተመለከተ ያላቸው ግንዛቤ ደግሞ እንደው ዝም y¸Ãsኝ አይነት ነው፡፡ በዞኑ ሰላም ለማሥፈን ላይ ታች የሚልን መንግሥት በማቀብ፣ ሰላምን ከተሣሣተ ቦታ ለማግኘት ደፋ ቀና ይላሉ፤ የተሣሣቱ ሰዎች ባቀበሏቸው ፍፁም ከተሣሣተ መረጃ ኮንግረሱን ለማሣሣት ችለዋል-ዶናልድ ፔይን፡፡ ለግንዛቤ ይረዳን ዘንድ በአሁኑ ወቅት የምሥራቅ አፍሪካን ወቅታዊ ሁኔታ በወፍ በረር መመልከቱ ጠቃሚ ይመስለናል፡፡ ከሶማሊያ እንጀምር፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሶማሊያ ባለፉት 16 ዓመታት አግኝታ የማታውቀውን ሰላም በማጣጣም ላይ ትገኛለች፡፡ ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ከማቋቋም አልፋ የሰላምና የእርቅ ኮንፈረንስ በማድረግ በሱማሊያ ጎሳዎች መካከል ለዓመታት ተፈጥሮ የነበረውን የርስ በርስ መጠፋፋት፣ በዚህም የተነሣ የተፈጠረውን ቁስል ለማጥገግ ደፋ ቀና በማለት ላይ ትገኛለች፡፡ ለዚህም ሰላም መገኘት ትልቁን መስዋዕትነት የከፈለው ፊት ለፊት አሸባሪዎችን በመጋፈጥ ድል የነሣው ጠንካራው የመከላከያ ሠራዊታችን ነው፡፡ ይህን አንፀባራቂ እርምጃ በመውሰድ ምስራቅ አፍሪካን እንደ አፍጋኒስታን የአሸባሪዎች መፈልፈያ ለማድረግ አስቦ የነበረውን አልቃይዳንና ተባባሪዎቹን አከርካሪ መስበር ችሏል፡፡ ውጤቱም አሜሪካን ከዚህ ቀደም በዚያው በሶማሊያ፣ አሁን በቅርቡ ደግሞ በአፍጋኒስታን ካደረገቻቸው ሽብርተኞችን የመደምሰስ እርምጃ በበለጠ አንፀባራቂ፣ የተዋጣለት ወታደራዊና ህዝባዊ ድል ተገኝቷል፡፡ ኢትዮጵያ በሽብርተኞች ላይ እየወሰደች ያለችው እርምጃ የራሷን ህልውና ከመጠበቅ የዜጎቿን ሰላምና ፀጥታ ከማረጋገጥ አኳያ ተገቢነት ያለው ነው፡፡ ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚደረገው የአሸባሪነት ትንቅንቅ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ እንድትሆን አድርጓታል፡፡ ይህ ተጋድሎ ምሥራቅ አፍሪካን ይበልጥ የተረጋጋ የሰላም ቀጣና አድርጎታል፡፡ ድርጊቱም የአሜሪካን የውጭ ፖሊሲ የሚቃረን ሣይሆን የሚደግፈው ነው፡፡ ትንሿ ሀገር ኤርትራ በኮንግረስ በፀደቀው ረቂቅ ሊግ ካሥፈነደቃቸው ወገኖች መካከል አንዷ ናት፡፡ ወራሪው የሻዕቢያ መንግስት ይህን ረቂቅ ህግ መደገፉ ብዙም የሚደንቅ ነገር ሊሆን አይችልም፡፡ ምክንያቱም ግል ነው፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በሶማሊያ ያደረገው አንፀባራቂ ወታደራዊ እርምጃ ገፈት ቀማሽ በመሆኑና ምሥራቅ አፍሪከን ለማተረማመስ እንደ መረማመጃ ይጠቀምባት የነበረችውን ሞቃድሾን ባላሰበውና ባልገመተው ፍጥነት ከእጁ መውጣቷና ረቂቅ ህጉ በኮንግረሱ መደቁ ሊያሥፈነድቀው ይችላል፡፡ በቅርቡም ከኢትዮጵያ ጦር የተራረፉትን (ዳሂር አዋይስን ጨምሮ) አሸባሪ የእስልምና ምክር ቤት አባላትን በግል በአሥመራ በመሰብሰብ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያWÃNN እስከጎዳ ድረስ ከዓለም አሸባሪ ድርጅቶች ጋር ያለውን የትግል አጋርነት የገለፀው ይህ የኤርትራ መንግሥት ባህርይ ለኢትዮጵያWÃN ለኢትዮጵያ መንግሥት አዲስ ባይሆንም አለምን ግን አስደንግጧል፡፡ የአሜሪካን መንግሥት ኤርትራን የአሸባሪ መንግሥታት ሊስት ውስጥ ለመክተት እያሰበ መሆኑም መንስኤው ይኸው ነው፡፡ ዶናልድ ፔይንና lHR-2003 ድጋፋቸውን የሰጡ የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት በሙሉ ይሄንን ልብ ሊሉት በተገባ ነበር፡፡ እንደ ኤርትራ ያሉ የአፍሪካ ቀንድን የጦርነት ቀጣና ለማድረግ የሚጥሩ መንግሥታትና የአሸባሪ ቡድኖችን ወደ ጎን ትቶ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት የምትጥረውን ጥንታዊት ሃገር ለመወንጀል መሯሯጥ አግባብ አለመሆኑ በእጅጉ በተረዱት ነበር፡፡ ይህንን አሸባሪ መንግስት (በ1991-92 በኢት×-ኤርትራ ጦርነት እንደታየው) ለመግታት አቅም ያላት ሀገር በምሥራቅ አፍሪካ ኢትዮጵያ ብቻ ናት፡፡ በህቡእና በግል በመደራጀትና እንዲሁም በመንግሥታት ደረጃ አሸባሪነትን መታገል ምሥራቅ አፍሪካን ይበልጥ የተረጋጋና ለኑሮ አመቺ የአለም ክፍል ለማድረግ ያስችላል፡፡ በዚህም የአሜሪካንም የውጭ ፖሊሲ አጋር መሆንን እንጂ በተቃራኒው መቆምን አያመለክትም፡፡ ዳርፉር በአሁኑ ወቅት የአለምን ትኩረት የሳበ ጉዳይ እየሆነ በመምጣት ላይ ይገኛል፡፡ በዚያ የሚደረገውን የእርስ በርስ ጦርነት የምሥራቅ አፍሪካን አካባቢ ያልተረጋጋ ወይም (volatile) ግጭቶች መቼ እንደሚከሰቱ ለምን እንደሚከሰቱ ለመተንበይ አስቸጋሪ ነው የሚለውን የምእራራቡ ዓለም ፖለቲከኞች ግምት እውነትነት አምነው እንዲቀበሉ ያደረጋቸው ክሥተት ሆኗል፡፡ ኢትዮጵያ በተናጠል እንዲሁም ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመተባበር የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግሥታት ሰላም አስከባሪ ወደ ዳርፉር እንዲገባ የሱዳንን መንግሥት በማግባባት ረገድ ከፍተኛ ሚና ስትጫወት መቆየቷ ይታወቃል፡፡ በአሁኑ ወቅትም የተባበሩት መንግሥታት በአካባቢው ሊያሠማራ ላቀደው ጠንካራ የመንግስታቱ ጦር ኢትዮጵያ አምስት ሺህ ወታደሮች ለማዋጣት ከመሥማማት ባሻገር ሠራዊቷ በተፈለገበት ጊዜ ወደ ቦታው እንዲንቀሳቀስ በተጠንቀቅ መቆሙን ለዓለም አሳውቃለች፡፡ ይህ የሀገራችን አቋም ከዓለም ህብረተሰብ ጎን በመቆም በአፍሪካ ሰላም ለማስጠበቅ ያላትን ጠንካራ ፍላጎት በድጋሚ ያረጋገጠ ሆኗል፡፡ ከአሜሪካ የውጭ ፖሊሲ አኳያ ይበል የሚያሰኝ እንደሆነ ለማወቅ ብዙ መመራመር አያስፈልግም፡፡ ከላይ በጥቂቱ ለመመልከት እንደሞከርነው ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ የአሜሪካን አጋር እንጂ የጎሪጥ ልትታይ የሚገባት አገር አይደለችም፡፡ ሁላችንም ልብ ልንል የሚገባን ጉዳይ ሀገራችን በምሥራቅ አፍሪካ አልፎ ተርፎም በአፍሪካ እየተጫወተች ያለችውን ገንቢ ሚና የቅድሚያ ተጠቃሚ ራሷ ሀገራችን ናት፡፡ በኤርትራ ቀጥሎም በሶማሊያ የተወሰዱት ወታደራዊ እርምጃዎች ሀገራችን ሉዓላዊነት ላይ አንዦቦ የነበረውን አደጋ ለመቀልበሥ እንጂ የአሜሪካንን አጋርነት ለመሻት የተወሰዱ አልነበሩም ወደፊትም በዚህ ሁኔታ የሚወስድ እርምጃ አይኖርም፡፡ አሁን በዳርፉር፣ በላይቤርያ እንዲሁም በብሩንዲ የኢትዮጵያ ሰራዊት የሰላም ማስከበር እንቅስቃሴ አህጉራዊ ግዴታውን ለመወጣትና አፍሪካ ወደ ሰላም የምታደርገውን የርስ በርስ ትብብር ለማጎልበት እንጂ የአሜሪካንን አጀንዳ ለማስፈፀም እንዳልሆነም ሊታወስ ይገባል፡፡ እንደውም አንዳንድ የሀገራችን የተናጠል እርምጃዎች አስቀድሞ በአሜሪካ መንግሥት ተቀባይነት ያልነበራቸው ነበሩ፡፡ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ለዚህ አንዱና ተጠቃሽ ጉዳይ ነው፡፡ ያለፈው የአሜሪካ መንግሥት የጉዳዩን መነሻ ሣይመረምር በደፈናው በሁለቱም ሀገሮች ላይ የመሣሪያ ማዕቀብ እስከመጣል ደርሶ ነበር እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል እንዲሉ አሁን ራሱ የአሜሪካን መንግሥት የኤርትራን መንግሥት አሸባሪ ሊስት ውስጥ ለማካተት እየተግደረደረ ይገኛል፡፡ በቅርቡም የኢትዮጵያ ጦር ወደ ሶማሊያ ድንበር አልፎ በተጠጋበት ግዜ ከወደ አሜሪካ ይደመጥ የነበረው መግለጫ የማስጠንቀቂያና ጦሩም ሥጋት ነው ያለውን ቡድን ከደመሰሰ በኃላ በአሥቸኳይ ሶማሊያን ለቆ እንዲወጣ የሚያሳስቡ ነበሩ፡፡ የምንግዜውም ጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን ግን አለምን ባስደመመ ፍጥነት ከመላው አለም የተሰባሰቡትን አሸባሪዎች ድምጥማጣቸውን አጥፍቶ ሶማሊያ መረጋጋት ስትጀምር የሰላም ብርሃን ሲፈነጥቅ የኢትዮጵያ ሰራዊት ለቆ መውጣት ያለበት የአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ሀይል ተጠቃሎ ሲገባ ብቻ ነው፡፡ በማለት ተማኖ አዘል መግለጫዎች ናቸው የሚደመጡት፤ ከዚያው ከአሜሪካ፡፡ HR-2003 ቢፀድቅ ተጎጂው ማን ነው? ረቂቁ ህጉ በሴኔቱ ድጋፍ አግኝቶ በፕሬዚዳንቱ ፊርማ ፀድቆ ህግ ሆኖ ቢወጣ፣ አስቀድሞ የሚጎዳው ከአሜሪካን መንግስት ድጋፍ ተጠቃሚ የሆነው ደሀው የሀገራችን ህዝብ ነው፡፡ በዕርዳታው የሚሰሩ ትምህርት ቤቶች፣ ክሊኒኮች መንገዶች መስተጓጎል የቅድሚያ ተጎጂ ያደርገዋል፡፡ ቀጥሎ የዚህ ረቂቅ ህግ ሰለባ የሚሆነው የራሷ የአሜሪካን መንግስት የውጪ ፖሊሲ ይሆናል፡፡ ከላይ በጥቂቱ እንደተመለከትነው ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ ሽብርን በፊታውራሪነት በመታገል ላይ የምትገኝ የአሜሪካን አጋር ሀገር ነች፡፡ በጥቅሉ የረቂቅ ህጉ መደቅ በሁለቱ ሀገሮች መካከል የሚኖረውን ወዳጅነት ይጎዳል፡፡ አሜሪካም በዞኑ የሚኖራትን ተሰሚነት ማቀዝቀዙ የግድ ይላል፡፡ የረቂቁ ህግ መደቅ ተጠቃሚውስ ማነው? ዶናልድ ፔይን የዚህ ቢል መጽደቅ አይጎዱም፡፡ ተጠቃሚም አይሆኑም፡፡ በአንዲት ደሀ አገር ሀገራቸው በሳቸው አነሣሽነት በፀደቀ ረቂቅ ህግ አማካኝነት ለመቅጣት በመሞከራቸው ሲመፃደቁ ለመኖር ካልሆነ በቀር ፋይዳ ያለው ጥቅም ለሀገራቸው አያስገኙም፡፡ ህጉን ለማፀደቅ ላይ ታች ከሚሉት ወገኖች መካከል በዋናነት የሚጠቀሱት ህገ መንግስቱን በመጣስ ተፈርዶባቸው የነበሩ የቅንጅት መሪዎች (ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ) በኮንግረሱ ፊት ምስክርነት በመስጠት ለህጉ ተግባራዊነት የበኩላቸውን ሚና ተጫውተዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች በቅርቡ ከመንግስት በተደረገላቸው ምህረት ከእስር ቤት መውጣታቸው ይታወሣል፡፡ የሀገር ሽማግሌዎች ለነሱ መፈታት ብዙ ደክመዋል፣ ህዝቡም በመፈታታቸው የተሰማውን ልባዊ ደስታ በተለያዩ መንገዶች ሲገል ቆይቷል፡፡ በብዙዎች ዘንድ ለኢትዮጵያ ፖለቲካዊ መቻቻል የመጀመሪያ ምዕራፍ አድርጎ የመመልከት ክስተትም ነበር፡፡ ለዚህ ሁሉ ድካምና ተስፋ ቀዝቃዛ ውሃ ቸለሱበት፡፡ መንግስት ላደረገላቸው ምህረት ምላሽ የሀገርን ሉዓላዊነት ለሚደፍር ህግ መደቅ ምስክርነት ሰጡ፡፡ የመንግሥትንና የሀገር ሽማግሌዎችን ድካም መና አስቀሩት፡፡ በሀገራቸው የሸበቡትን አፋቸውን ዶናልድ ፔይን ፊት ከፈቱት ለበጎ ሣይሆን ለዕኩይ ዓላማ ተባባሪ ለመሆን ግዜ አልወሰደባቸውም፡፡ የመረጣቸው ህዝብ በሀገር ውስጥ አንዳች ነገር ከነሱ ለመሥማት በሚፈልግበት ሰዓት ጥለውት ወደ አሜሪካን ለመሄድ ኤምባሲውን አጣበቡት ሄደውም የመረጣቸውን ህዝብ ለሚጎዳ ህግ መደቅ መሥክርነት አንደበታቸውን ከፈቱ፡፡ ሌላው የረቂቅ ህግ መደቅ ሌት ተቀን ደፋ ቀና ከሚሉት ዶናልድ ፔይን ጎን አብረው ተፍ ተፍ ከሚሉት ወገኖች መካከል የራሳቸው የዶናልድ ፔይን የሙሉ ሰዓት አማከሪ የሆኑት ኢትዮጵያዊው ዶክተር ዳኜ ናቸው፡፡ እኚህ ሰው ለረቂቅ ህጉ መጽደቅ ከፍተኛውን ሚና ለመጫወታቸው ምንም ጥርጥር የለውም ከሣቸውም ጎን ለሀገር ቀና የማያስቡ የዲያስፖራው አባላት ድጋፋቸውን ሰጥተዋል፡፡ የኤርትራ መንግሥት ሌላው ከዚህ ረቂቅ ህግ መጽደቅ ተጠቃሚ ለመሆን እየተውተረተረ የሚገኝ አሸባሪ መንግሥት ነው፡፡ ከዚህ ጎን የሚሰለፉት ኦነግና የኦጋዴን ነፃ አውጭ የመሣሠሉ አሸባሪ ድርጅቶች ናቸው፡፡በአጠቃላይ ከዚህ ረቂቅ ህግ ተጠቃሚ ለመሆን የሚጥሩት ወገኖች ለሀገራቸውና ለህዝቦቻቸው ቀና የማያስቡ የለየላቸው የሀገር ጠላቶች ናቸው፡፡ በመጨረሻ ረቂቅ ህጉ ለመደቅ ያለውን ዕድል ላይ ጥቂት ብለን እንለያይ ይህ ረቂቅ ህግ-ህግ ሆኖ ለመውጣት በመጀመሪያ ወደ ሴኔቱ ቀርቦ አብላጫ ድም በማግኘት መጽደቅ ይኖርበታል፡፡ ከዚያም በፕሬዝዳንቱ ፊርማ ሲያገኝ ብቻ ነው ህግ ሆኖ ተግባራዊ መሆን የሚችለው፡፡ ኮንግረሱ ረቂቅ ህጉን ከማደቁ በፊት የአሜሪካን መንግሥትን አቋም ለማብራራት ቀርበው የነበሩት ጃንዳይ ፍሬዘር በጉዳዩ የመንሥታቸውን አቋም በግል አስቀምጠዋል፡፡ ከዚህም በመነሣት ረቂቅ ህጉ የሁለቱን ምክር ቤቶች ይሁንታ ቢያገኝ እንኳ የፕሬዝዳንቱን ፊርማ ለማግኘት የማይችል መሆኑን ከወዲሁ መተንበይ ይቻላል፡፡ |
|
|
|
|