ነሃ ኢንተርናሽናል የተባለ የህንድ ኩባኒያ በኢትዮጵያ በአበባው ዘርፍ ሊሳተፍ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ ግንቦት 5/2000/ ዋኢማ/ ነሃ ኢንተርናሽናል የተባለ የህንድ ኩባንያ በኢትዮጵያ ሁለት የአበባው ማምረቻዎች ማእከላትአንደሚያቋቁም ተገለጸ።

ቶፕ ኒውስ የተባለ የአገሪቱን የዜና ድረ-ገጽን ጠቅሶ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንደዘገበው፤ ኩባኒያው በኢትዮጵያ የአበባ ማምረቻ ማእከላት ለማቋቋም ከውሳኔ ላይ ደርሷል።

በኢትዮጵያ የሚያቋቁመው የአበባ ማምረቻ ማሳ 56 ሄክታር መሬት ሲሆን፤ 12 ሄክታሩ ግሪን ሃውስ የሚገነባበት እንደሆነ ዘገባው አመልክቷል።

ነሃ ኢንተርናሽናል ኩባኒያ በህንድ አበባን በማምረትና ወደውጭ በመላክ የተሰማራ ኩባኒያ መሆኑን ቶፕ ኒውስን ጠቅሶ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል።