የአፍሪካ ኅብረት የሰላምና የፀጥታ ምክር ቤት በኮቲዲቭዋር ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ተወያየ

አዲስ አበባ ጥቅምት 8/1999 የአፍሪካ ኅብረት የሰላምና የፀጥታ ምክር ቤት 64ኛው ስብሰባ የኮቲዲቭዋርን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ በቀረበው ሪፖርት ላይ ውይይት አካሄደ።

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመን በር አልፋ ኦማር ኮናሬ እ.ኤ.አ ከሰኔ እስከ ጥቅምት 2ዐዐ6 የነበረውን የኮቲዲ ቭዋርን የሰላምና የፀጥታ ሁኔታ በተመለከተ ትናንት ለምክር ቤቱ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡

በስብሰባው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ጨምሮ የኮትዲቭዋሩ ፕሬዚዳንት ሎራን ባግቦ፣ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ታቦ ምቤኪ፣ የሴኔጋሉ ፕሬዚዳንት አብዱላይ ዋዲ፣ የጋቦኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ባንጐ፣ የቡርኪናፋሶ ፕሬዚዳንት ብሌን ኮንወሬ የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀ መንበር የኮንጐ ብራዛ ቪል ፕሬዚዳንት ዴኒስ ሳሶ ኒጌሶ እና ሌሎች የመንግሥታት ወኪሎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ሊቀመንበሩ ትናንት በአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ በተካሄደው የኅብረቱ የሰላምና የፀጥታ ምክር ቤት 64ኛ ስብሰባ ላይ ያቀረቡት ሪፖርት እንደሚያመለክተው፤ ከ52ኛው የምክር ቤቱ ስብሰባ በኋላ የኮቲዲቭዋር የሰላምና የፀጥታ ሁኔታ እየተሻሻለ መምጣቱን ጠቁሞ፤ እ.ኤ.አ ካለፈው ነሐሴ 1/2ዐዐ6 ወዲህ ግን የፀጥታው ሁኔታ መደፍረሱን ገልጿል፡፡

የሀገሪቱን ሰላም ለማረጋጋትና የፍትህ ሥርዓቱን ለማስጀመር ተዘዋዋሪ ችሎቶችን እ.ኤ.አ ከሐምሌ 17/2ዐዐ6 ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ ሥራ ጀምረው እንደ ነበር ሪፖርቱ ጠቅሶ፤ የፍትህ ሥርዓቱን ለማስጀመር የተደረገውን ጥረት የአይቮ ሪኮስት ሕዝባዊ ግንባር የተባለው ተቃዋሚ ፓርቲ እንዳልተቀበለው አስታውቋል፡፡ በዚህም በሀገሪቱ ግጭት መቀስቀሱን ጠቁሟል፡፡

የሀገሪቱ መንግሥት የተፈጠረውን ውጥረት ለማብረድ ጥረት ማድረጉንና ተዘዋዋሪ ችሎቶችን ሥራ ለማስቀጠል መንቀሳቀሱን የቀረበው ሪፖርት ያመለክታል፡፡የታጠቁ ኃይሎችን የማስፈታትና መልሶ የማቋቋም እንቅስቃሴ እ.ኤ.አ ከሐምሌ 26/2ዐዐ6 ተጀምሮ እስከ ነሐሴ መጀመሪያ ብቻ 88ዐ ታጣቂዎች ትጥቅ መፍታታቸውና የመልሶ ማቋቋም ሥራ መካሄዱን ሪፖርቱ ያስረዳል፡፡

ሪፖርቱ የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ እ.ኤ.አ ጥቅምት 6/2ዐዐ6 ባካሄደው ልዩ ስብሰባ የሽግግሩ መንግሥት እ.ኤ.አ ጥቅምት 31/ 2ዐዐ6 የሚያበቃ መሆኑን ጠቅሷል፡፡ አሁን ባለው የሀገሪቱ ሁኔታ የሽግግሩን መንግሥት የሥራ ጊዜ በተያዘለት ወቅት ማጠናቀቅ የማይችል መሆኑን ሪፖርቱ አስገንዝቦ የቆይታ ጊዜው ስለሚ ራዘምበት ሁኔታ አስፈላጊነት ጠቅሷል፡፡

አሁን ባለው የሀገሪቱ ሁኔታ ምርጫ ማካሄድ እንደማይቻል ጠቁሞ፤ ለምርጫው በቂ ዝግጅትም ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልጿል፡፡ የሽግግሩ ዘመን እ.ኤ.አ ከሕዳረ 1/2ዐዐ6 ጀምሮ ከ12 ወራት ባልበለጠ ጊዜ እንዲራዘም የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ መወሰኑን ጠቅሷል፡፡

የመራጮች ምዝገባ ለማካሄድ፣ ትጥቅ የፈቱ ኃይሎችን በማቋቋምና የሀገሪቱን የጦር ኃይል በአዲስ መልክ ለማደራጀት፣ መንግሥታዊ መዋቅሮች በመላ ሀገሪቱ ለማቋቋምና ለምርጫ የሚያስፈልጉ የቴክኒክ ሥራዎች ለመሥራት የሽግግሩ ዘመን በአንድ ዓመት መራዘሙን የምዕራብ የአፍሪካ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ እንዳመነበት ሪፖርቱ ያስረዳል፡፡

የኢኮኖሚ ማኅበረሰቡ ለአንድ ዓመት የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሎራን ባግቦ የሀገሪቱ መሪ እንዲሆኑና ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢኮኖሚ ማኅበረሰቡ የቀረቡ ሃሳቦችንና ውሳኔዎችን የማስፈጸም ሙሉ ሥልጣን እንዲኖረው መወሰኑን ጠቁሟል፡፡

የአፍሪካ ኅብረትና የክፍለ አህጉሩ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ በተቃዋሚዎችና በመንግሥት መካከል ለሚፈጠሩ አለመስማ ማቶች የማደራደር ተግባር እንዲያከናውኑ መወሰኑን የሊቀመንበሩ ሪፖርት ያመለክታል፡፡ ምክር ቤቱ በቀረበው ሪፖርት ላይ በዝግ ስብሰባ ተወያይቶ ለሀገሪቱ ሰላምና ፀጥታ የሚጠቅሙ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል፡፡