በትግራይ የአመራር አካላት በመልካም አስተዳደር የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት ተኩረት ሰጥተው እነደሚሠሩ ተገለፀ

መቀሌ ጥቅምት 2/1999/ዋኢማ/ በተያዘው አዲስ ዓመት የመንግሥት አመራር አካላት በመልካም አስተዳደርና በፍትሕ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት ትኩረት ሰጥተው መሥራት እንዳለባቸው የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አስገነዘቡ።

ርዕሰ መስተዳደሩ አቶ ጸጋይ በርሄ ለወረዳ አፈ ጉባኤዎችና ዋና አስተዳዳሪዎች የምክርቤት አሰራረን አስመልክቶ ዛሬ በመቀሌ ከተማ የተጀመረውን ስልጠና ሲከፍቱ እንዳስገነዘቡት፤ ለልማት ዋንኛ እንቅፋት የሆኑትን በመልካም አስተዳደርና በፍትህ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት በየደረጃው ያሉ ህግ አውጪ፣ ህግ ተርጓሚ የሥራ አስፈጻሚ አካላት የበኩላቸው ድርሻ መወጣት ይጠበቅባቸዋል።

በአገሪቱ ፍትሐዊ ሥርዓትን መመሥረት ከእያንዳንዱ ዜጋ የሚጠበቅ ተግባር ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ የህዝቡን የመልካም አስተዳደርና የፍትሕ ጥማት ለማርካት የሥራ አስፈጻሚ አካላት ትኩረት ሰጥተው መሥራት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

መልካም አስተዳደር ማሰፈን ሁለገብ ሥራ መካናወን ማለት ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ፣ ከአርሶ አደሩ በቀጥታ የሚገናኙት የኤክስቴንሽን ሠራተኞችና የአመራረ አካለቱ ግንኙነት መልካም ሊሆን ይገባል ብለዋል።

ለአመራር አካላቱ የተዘጋጀው ስልጠናም በህገ መንግሥቱ የተቀመጠውን የሥራ ኃላፊነት ተርድተው የህዝቡን መልካም አስተዳደር፣ፍትሕና ልማትን ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረተ እንደሚያጠናክር ገልጸዋል ።

የሽግ አውጭውን ፣ሕግ አስፈፃሚውንና ሕግ ተርጓሚውን አካላት ተደበላልቆ የመሄድ አዝማሚያ ለማስቀረትና የየራሳቸውን የሥራ ነጻነት ጠብቀው ተደጋግፈው በመሥራት የበለጠ ውጤትማ ለመሆን እንደሚረዳ ርዕስ መስተዳድሩ ስረድተዋል።

ምክርቤቱ የሥራ ዕቅድ አውጥቶ፣በጀት መድቦ በማጽደቅ ሥራ አፈጻጸሙን በሚቆጣጠርበት ጊዜ ለሥራ አስፈጻሚው የማይታዩት ጉድለቶችን አጉልቶ መወንጀል ሳይሆን ስህተቶችን እንዲስተካከሉ በማድረግ መደገፍ እንደሚያስፈልግም አመልክተዋል።

የክልሉ ምክርቤት አፈ ጉባኤ ዶክተር ወልዴሩፋኤል አለማዮህ በበኩላቸው የስልጠናው ዓላማ ሦስቱ የመንግሥት አካላት ያላቸውን ደከማ ጎን በማረም ህዝቡን በማሳተፍ ድህነትን በጋራ ለማጥፋት ርብርብ ለማድረግ እንደሚያስችል አስታውቀዋል።

የክልሉ ምክርቤት ጽሕፈት ቤት ባዘጋጀውና ለሁለት ቀናት በሚቆየው ሥልጠና ተሳታፊዎቹ በአገራዊና ክልላዊ ህገ መንግሥት የስልጣን ክፍፍል፣ባልተማከለ አስተዳደር የምክርቤቶችን ድርሻ ማጠናከር ፣በወረዳ አደረጃጀትና አስተዳደር ረቂቅ ደንብ እንደሚወያዩና ያለፈው የወረዳ አስተዳደር ምክርቤቶች አሰራር እንደሚገመም ዋልታ ኢንፎርሜሸን ማዕከል ዘግቧል።