|
የመምህራን የደረጃ እድገት መፈቀዱ መንግስት ለሙያው የሰጠውን ክብር እንደሚያሳይ ተገለጸ |
አሶሳ መስከረም 29/1999/ዋኢማ/መንግስት ተቋርጦ የቆየው የመምህራን የደረጃ እድገት መፍቀዱ የመምህሩን የኢኮኖሚ አቅም ከማጠናከር ባሻገር ብቁ ዜጋን ለማፍራት ለሚያደርገው ጥረት አጋዥ ነው ሲል የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የመምህራን ማህበር አስታወቀ፡፡ የማህበሩ ዋና ፀሐፊ አቶ ጌታሁን ተክለማርያም የደረጃ እድገት መፈቀዱን አስመልክተው ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንዳስታወቁት የደረጃ እድገቱ መፈቀዱ መንግስት የመምህሩን የኢኮኖሚ አቅም በማጎልበት የትምህርት ፖሊሲው በአግባቡ በመተግበር የበኩሉን ሚና እንዲጫወት ጠቀሜታው የጐላ ነው ብለዋል፡፡ ስራ አክባሪና አገር ወዳድ ዜጋን በመፍጠር ረገድ መምህሩ ዋነኛ ሞተር ነው ያሉት የማህበሩ ዋና ጸሃፊ የተደረገው የደረጃ እድገት መንግስት ለመምህሩ የሰጠውን አክብሮትና ለሙያው ያለውን ክብር በግልጽ ያሳያል ማለታቸውን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል፡፡ |
|
|
|
|