|
ለአሥር ዓመታት የሚያገለግል የመቀሌ ከተማ ማስተር ፕላን ሥራ መጠናቀቁ ተገለፀ |
መቀሌ መስከረም 29/1999/ዋኢማ/የመቀሌ ከተማ የአሥር ዓመት ማስተር ፕላን ፕሮጀክት ሥራ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት መዘጋጀቱን የከተማዋ ማዛጋጃቤት አስታወቀ ። የማዛጋጃ ቤቱ ህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ዮሃንስ ሐጎስ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንዳስታወቁት ጥር 1996 የተጀመረው የማሰተር ፕላኑ ሥራ በቅርቡ የተጠናቀቀ ሲሆን በበተያዘው ዓመት በክልሉ ምክርቤት ከጸደቀ በኋላ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል። ማስተር ፕላኑ በዋናነት የመሬት አጠቃቀም መወሰኛ ፣የከተማዋ ዋናና የውስጥ ለውስጥ መንገዶች፣የመኖሪያቤት መገንቢያ ቦታዎችን፣ የቀለበት መንገዶችንና በርካታ የተፋሰስ ሥራዎችን ያካተተ መሆኑን ገልጸዋል ። በማስተር ፕላኑ በከተማዋ ያለውን ከፍተኛ የመኖሪያ ቤቶች ችግር ለማቃለል የሚያስችል ከ900 ሄክታር በላይ መሬት መከለሉን ባለሙያው አመልክተው፣በተጨማሪም በከተማዋ ወደፊት ሊፈጠር የሚችለውን ዕድገት ለማሰተናገድ የሚያስችል 70 ሄክታር ቦታ በተጠባባቂነት መያዙን ተናግረዋል። ማሰተር ፕላኑ ለአሥር ዓመታት እንዲያገለግል ታስቦ ከመሠራቱም ማሻገር የከተማዋን ማሕበራዊ ፣ምጣኔ ሀብታዊና፣ፖለቲካዊ ሁኔታዎችን ያገናዘበና አዲስ ለሚመጡ የቴክኖሎጂ ዕድገት ለውጦችን ግምት ውስጥ ያስገባ ነው ብለዋል ። የማስተር ፕላን ፕሮጀክቱ በየጊዜው እየተገመገመ የሚሻሻል ሲሆን ባጠቃላይ ለ20 ዓመታት የሚያገለግል የዕድገት ፕላን መሠረት ያለው መሆኑን አቶ ዮሃንስ አስረድተዋል። |
|
|
|
|